በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮምያና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሚታዩ ችግሮች ዘላቂ እልባት ተጠየቀ


“መቶ ሰማኒያ ወይም መቶ አርባ ሰው ሲሞት፤ ሌላ አገር ቢሆን ባንዲራ ዝቅ ተብሎ የአገሪቷ ብሔራዊ ሃዘን ይደረጋል። ሰው ነው፤ ታዳጊዎች ናቸው፤ ልጆች ናቸው ነገ አገር ሊመሩ የሚችሉ ናቸው የሞቱት። እንዴት ብዬ ልነግርህ እንደምችል አላውቅም። ሰው ሲሞት አገር የሚያስተዳድር ዝም ማለት? ምን እንደምል አላውቅም። አስቸጋሪ ነው።”

የአዲስ አበባንና የፊንፊኔ ዙሪያ ዞኖችን የከተሞች ማስፋፊያ እቅድ ተንተርሶ ከተቀሰቀሰውና በኦሮምያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ትምሕርት ቤቶች ተማሪዎች ሲያካሂዱ የቆዩት የተቃውሞ እንቅስቃሴ የክልሉ መንግስት እቅዱን መተዉን ካስታወቀም በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም መቀጠሉ እየተዘገበ ነው።
በምዕራብ ሸዋ ዞን በጅባት ወረዳ የሸነን ከተማ ከትላንት በስቲያ በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት በጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመቶ የቆሰለ አንድ የ15 ዓመት ወጣት በዛሬው ዕለት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ።
በሌላ በኩል የተቃውሞ ሰልፎቹን ተከትሎ ባሁኑ ወቅት በእስር ላይ የሚገኙት የአመራር አካላት በቅርብ ቤተሰቦቻቸው አባላት እንዲጎበኙ መፈቀዱን ያረጋገጠው ተቃዋሚው የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግሬስ
“አዎንታዊ” ያለውን እርምጃ አወድሶ፤ ለችግሩ ሁነኛና ዘለቄታ ያለው እልባት ያበጁ ዘንድ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝንና ሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት ጠይቋል።
ከኦሮምያ ውጪ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች እየታዩ ላሉ ላላቸው ችግሮች ጭምር ሁሉንም ወገኖች ያሳተፈ ግልጽ ንግግር ነው መደረግ ያለበት፤ ሲል ኦፌኮ ወቅታዊውን ሁኔታ የገመገመበትን አስተያየት ለአሜሪካ ድምጽ ሰጥቷል።
በኦሮምያና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሚታዩ ችግሮች ዘላቂ እልባት ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:27 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG