በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ አንዳንድ ከተሞች ተቃዉሞ ቀጥሏል


የአዲስ አበባና የፊንፌኔ ዙሪያ የተቀናጄ የልማት እቅድ ወይም የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን የተባለዉን በመቃወም በህዳር ወር በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ ከሁለት ወር በላይ ማስቆጠሩ ነዉ።

በኦሮሚያ በምስራቅ ወለጋ ዞን በወለጋ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ ዞን ዛሬ በተካሄደ ሕዝባዊ ተቃዉሞ የአንድ ወጣት ሕይወት ማለፉ ታዉቋል።

በምስራቅ ሃረርጌ ዞን በሚኤሶ ወረዳ የተጀመረዉ የተቃዉሞ ሰልፍ ደግሞ ሰባተኛ ቀኑን መያዙን በዚያዉ መጠን እስራት ድብደባና ሌሎች በደሎች መቀጠላቸዉን ነዋሪዎች ለአፋን ኦሮሞ ዘጋቢዎች ገልጸዋል። በሌላ በኩል በምስራቅ ሸዋ ጉደር ከተማ ትላንት በተካሄደዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የጸጥታ ሃይሎች የጥቃት እርምጃ መዉሰዳቸዉም ታዉቋል። በየአካባቢዉ ያነጋገርናቸዉ የመንግስት ባለስልጣናት ተወሰደ የተባለዉን የሃይል እርምጃ ያስተባበሉ ሲሆን፥ በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ባለስልጣናቱን ለማነጋገር የተደረገዉ ጥረት አልተሳካም።

የድምጽ ፋይሉን በመጫን ዝርሩን ያድምጡ።

በኦሮሚያ አንዳንድ ከተሞች ተቃዉሞ ቀጥሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:32 0:00

XS
SM
MD
LG