በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰላማዊ ትግሉ “አሁንም ተስፋ አስቆራጭ አይደለም” - አቶ ጥላሁን እንደሻው

ፋይል - የመድረክ ደጋፊዊች በኦሮምያ ክልል ሰልፍ በተሳተፉበት ጊዜ የተነሳ ፎቶ እአአ 2010
ፋይል - የመድረክ ደጋፊዊች በኦሮምያ ክልል ሰልፍ በተሳተፉበት ጊዜ የተነሳ ፎቶ እአአ 2010

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ ሰሞኑን ኦሮሚያ ውስጥ በተፈጠረው ተቃውሞና አለመረጋጋት ምክንያት “ተገደለ” ያሉት ሰው ቁጥር ሰማንያ ዘጠኝ መድረሱን የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊው አቶ ጥላሁን እንደሻው ገልፀዋል።

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ ሰሞኑን ኦሮሚያ ውስጥ በተፈጠረው ተቃውሞና አለመረጋጋት ምክንያት “ተገደለ” ያሉት ሰው ቁጥር ሰማንያ ዘጠኝ መድረሱን የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊው አቶ ጥላሁን እንደሻው ገልፀዋል።

አቶ ጥላሁን ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ ሰማንያ ዘጠኝ ሰው ስለመገደሉ ተጨባጭ ማስረጃ፣ ስምና አድራሻው የደረሣቸውና በተጨባጭ እናውቃለን ያሉትን እንጂ የሚያምኑት ከመቶ ሰው በላይ መገደሉን እንደሆነ አመልክተዋል።

“ኢሕአዴግ አሁን ስለ አዲስ አበባ ማስተር ፕላን ከመናገር ይልቅ ማድረግ ያለበት ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር ተቀምጦ በሕገመንግሥቱ አንቀፅ 49 የተደነገገው ‘የኦሮምያ ክልል፣ የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀምንና የመሣሰሉትን ጉዳዮች…’ መነጋገር ነው” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት (መድረክ) አዲስ አበባ ውስጥ ባዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ የተገኘ ህዝብ እአአ 2014 ዓ.ም. [ፎቶ ፋይል - ሮይተርስ]
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት (መድረክ) አዲስ አበባ ውስጥ ባዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ የተገኘ ህዝብ እአአ 2014 ዓ.ም. [ፎቶ ፋይል - ሮይተርስ]

ኢሕአዴግ የፓርላማውን መቀመጫ ሙሉ በሙሉ በተቆጣጠረበት ባለፈው ግንቦት በተካሄደው ምርጫ ማግስት ተቃዋሚዎችን እንደሚያሣትፍ የተናገረውን ለመተግበር ምን ያህል እየተንቀሣቀሰ እንደሆነ ተጠይቀው “ይህ አባባል ቀደም ሲልም የነበረ፤ በቃላት ብቻ የሚነገር ነው” ብለዋል።

የሰላማዊ ትግሉ ተስፋ አሁንም ተስፋ አስቆራጭ አይደለም ያሉት የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር እና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያው ኃላፊ አቶ ጥላሁን እንደሻው ሌሎችም የኅብረተሰቡ ክፍሎች ከጎናቸው እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ለአጭር ዘገባና ለሙሉው ቃለ ምልልሶች የተያያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ።

ሰላማዊ ትግሉ “አሁንም ተስፋ አስቆራጭ አይደለም” - አቶ ጥላሁን እንደሻው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:51 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ከመድረክ ምክትል ሊቀመንበር እና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያው ኃላፊ አቶ ጥላሁን እንደሻው ጋር የተደረገ ሙሉ ቃለ-ምልልሱንም ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምፅ ፋይል ይጫኑ።

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG