በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መድረክ ሰልፉን አዛወረ


መድረክ
መድረክ

በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተወሰዱ የኃይል እርምጃዎችንና የተፈፀሙ ግድያዎችን ለማውገዝ በሚል ለዛሬ ጠርቶት የነበረ ሰልፍ ዕውቅና ባለማግኘቱ ጥያቄውን በድጋሚ ለማቅረብ መወሰኑን መድረክ አስታውቋል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:01:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተወሰዱ የኃይል እርምጃዎችንና የተፈፀሙ ግድያዎችን ለማውገዝ በሚል ለዛሬ ጠርቶት የነበረ ሰልፍ ዕውቅና ባለማግኘቱ ጥያቄውን በድጋሚ ለማቅረብ መወሰኑን መድረክ አስታውቋል፡፡

መድረክ ትናንት ባካሄደው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ስብሰባ ነው ውሣኔውን ያሳለፈው፡፡

የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በሰጡት መግለጫ የሰልፉ ዓላማ ሲያብራሩ ሕገወጥ ግድያዎችንና ሕገ መንግሥታዊ የሆነውን ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግን ነፃነት በመፃረር የተወሰዱ የኃይል እርምጃዎችን ለመኮነን እና ለዚህም ለተሰዉት ወገኖቻችን ያለንን ክብር ለመግለፅ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደር ለሰልፉ ዕውቅና እንዳይሰጥ ያደረጉትን ምክንያቶች ሲዘረዝር “ሰልፉ የሚያልፍባቸው አካባቢዎች በልማት ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ ያለባቸውና በርካታ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት የሚገኙባቸው መሆናቸውን ገልፆ “እንዲሁም አሁን ባለው የወቅቱ ሁኔታም ጥያቄውን ተቀብለን ዕውቅና ለመስጠት እንቸገራለን” ብሏል፡፡

መድረክ ሰልፉን ለመቼ እንዳሰበ አልተገለፀም፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG