በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መድረክ በኦሮምያ ጉዳይ ባለ አምስት ጥያቄ መግለጫ አወጣ


መድረክ
መድረክ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ዛሬ ባለአምስት ጥያቄ መግለጫ አውጥቷል፡፡

መድረክ በኦሮምያ ጉዳይ ባለ አምስት ጥያቄ መግለጫ አወጣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:47 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ዛሬ ባለአምስት ጥያቄ መግለጫ አውጥቷል፡፡

ከመድረክ የሕዝብ ግንኙነት ጉዳይ መምሪያ የወጣው ይህ መግለጫ “ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን በማሠርና በማንገላታት የኦሮሞን ሕዝብ ሰላማዊና ሕጋዊ ትግል መግታት አይቻልም” የሚል ነው፡፡

መድረክ ታሥረዋል ወይም በቁም እሥር ይገኛሉ ብሎ የአሥር የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ መሪዎችን የስም ዝርዝር ካወጣበት መግለጫው ውስጥ ጥያቄዎቹና ጥሪው እንደሚከተለው ይነበባል፤

“ … 1ኛ፡- የሕዝቡ ሰላማዊ ጥያቄዎች በሚነሱባቸው አከባቢዎች ጥያቄዎቹን በኃይል ለማፈን ተሰማርቶ የሚገኘው የጸጥታ ኃይል እየፈጸማቸው የሚገኙት የግዲያ፣ የእስራትና የማንገላታት እርምጃዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ፣

2ኛ፡- በዚሁ ሰላማዊ የሕዝብ ትግል ምክንያት ሕዝቡን ቀስቅሳችኋል በምል ሰበብ ለእስራት የተዳረጉት ከዚህ በላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም የኦፌኮ/መድረክ አባላትና በሰላማዊ ትግሉ በመሳተፉቸው ምክንያት ለእስራት የተዳረጉት ዜጎቻችን በሙሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣

3ኛ፡- በሰላማዊ የመብት ጥያቄ በመሳተፋቸው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የተገደሉ ወገኖቻችን ቤተሰቦች ተገቢው ካሳ በመንግሥት እንዲከፈላቸው፣

4ኛ፡- በሰላማዊ ዜጎች ላይ የግዲያና የማንገላታት ተግባራትን የፈጸሙ አካላት ለሕግ እንዲቀርቡ፤

5ኛ፡- ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መንግሥት ከኦፌኮ/ መድረክና ከሌሎችም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ካለአንዳች ቅድመሁኔታ በመወያየትና በመደራደር ለሕዝቡ ፍትሀዊና ሕጋዊ ጥያቄ በአስቸኳይ ሕገመንግሥታዊ ምላሽ መስጠት ጊዜ ሳይሰጠው ተግባራዊ መሆን የሚገባቸውና አማራጭ የሌላቸው የችግሩ መፍትሔዎች ስለሆኑ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲደረጉ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ ተመሳሳይ ጭቆናና አፈና እየተፈጸመበት የሚገኘው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ወንድሙ የሆነ ው የኦሮሞ ሕዝብ ባነሳቸው ሕጋዊ ጥያቄዎች ምክንያት እየተፈጸመበት ያለውን ግፍና በደል ሊያወግዘውና የትግል አጋርነቱን ሊያረጋግጥለት ይገባል እንላላን፡፡”

መድረክ የኦፌኮ መሪዎች በእሥር ላይ እንደሚገኙ በመጥቀስ ስማቸውን በዘረዘረበት የመግለጫው ክፍል እንዲህ ብሏል፡፡

“… የኢህአዴግ አገዛዝ ሰሞኑን ያሰራቸው የኦፌኮና የመድረክ የአመራር አባላት ማለትም፡-

1ኛ፡- አቶ በቀለ ገርባ የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር፣
2ኛ፡- አቶ በቀለ ነጋ የኦፌኮ ዋና ጸሐፊና የመድረክ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፤(በቁም አሥር ላይ የሚገኙ)
3ኛ፡- አቶ ደጀነ ጣፋ የኦፌኮ ም/ዋና ጸሐፊ፣
4ኛ፡- አቶ ደስታ ድንቃ የመድረክና የኦፌኮ የወጣቶች ሊግ ሊቀመንበርና የኦፌኮ የኦዲት ኮሚቴ አባል፣
5ኛ፡- አቶ ጉርሜሳ አያኖ የኦፌኮ የወጣቶች ሊግ ም/ሊቀመንበርና የመድረክ የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ አባል፣
6ኛ፡- አቶ አዲሱ ቡላላ የኦፌኮ ወጣቶች ሊግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣
7ኛ፡- አቶ ደረጀ መርጋ የኦፌኮ የወጣቶች ሊግ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፣
8ኛ፡- አቶ ዓለሙ አብዲሳ የኦፌኮ ወጣቶች ሊግ ዋና ጸሐፊ፣
9ኛ፡- አቶ ጣሕር -------- የኦፌኮ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣
10ኛ፡- አቶ እስማኤል ----- በኢሉባቦር ዞን የዳርሞ ወረዳ የኦፌኮ ተጠሪ እና ሌሎችም በርካታ የኦፌኮ/መድረክ አባላትና በሰላማዊ ትግሉ በመሳተፋቸው ከመቶ በላይ የተገደሉትና በሺዎች የታሰሩት ወገኖቻችን ጥያቄዎቻቸውና ትግላቸው ሕገመንግሥታዊ ድንጋጌን መሠረት ያደረገና በሰላማዊ አግባብ የተጀመረ መሆኑን እኛ ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳንሆን መላው ዓለምም የሚያውቀው እውነት ነው፡፡…”

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ሰሞኑን ይሰጧቸው በነበሩ መግለጫዎች የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሕዝብ ካልተቀበለው ተግባራዊ እንደማይደረግ መናገናቸውና ኦሮምያ ውስጥ እየታየ ያለው ሁኔታ “የጥፋት ኃይሎች” ሲሉ በጠሯቸው የተቀነባበረ እንደሆነ በመግለፅ መንግሥቱ “የማያዳግም እርምጃ” እንደሚወስድ ሲያውቁ ቆይተዋል፡፡

የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊው አቶ ጥላሁን እንደሻው ለቪኦኤ የሰጡትን መግለጫ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG