በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመድረክ አስቸኳይ ጉባዔ


መድረክ
መድረክ

በቅርቡ የተካሄደውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ሂደትና ውጤት እንደማይቀበለው ተቃዋሚው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ ጉባዔ በይፋ አስታውቋል።

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ - የመድረክ ሊቀመንበር
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ - የመድረክ ሊቀመንበር

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:03 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በቅርቡ የተካሄደውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ሂደትና ውጤት እንደማይቀበለው ተቃዋሚው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ ጉባዔ በይፋ አስታውቋል።

“ኢሕአዴግ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጧል” የሚለው የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ አነጋገር አምባገነኖችን ያበረታታ ነው፤ ሲልም መድረክ ተችቷል።

በሙስሊሙ ኅብረተሰብ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ በሌሎች የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላትና በጋዜጠኞች ላይ በቅርቡ የተላለፈውን ፍርድ ፍትሐዊ ያልሆነ፤ ኢሕአዴግ በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ጣልቃ እንደሚገባ የሳየ ነው ብሏል መድረክ፡፡

ሰላማዊ ትግላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያስታወቁት የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከሚቀጥለው ጉባዔው በኋላ መድረክ እንደሚዋሃድ ጠቁመዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG