ዋሽንግተን ዲሲ —
ኢራን፣ የሚሳይል ፕሮግራሟም ሆነ በዚህ ሳምንት ያደረገችው ሙከራ፣ ቀደም ሲል ከስድስቱ ኃያላን ጋር የደረሰችውን የኑክሊየር ስምምነት እንደማይጥስ አስታወቀች።
ኢራን በኑክሊየር ፕሮግራሟ እንደምትገፋበትና ዓላማውም እራሷን ለመከላከል የሚውል መሆኑን፣ መንግሥታዊው የኢራን መገናኛ አውታር የውጩ ጉዳይ ሚኒስቴርን ቃል-አቀባይ ሁሴን ጃብሪ አንሳሪን ጠቅሶ ዘግቧል።
ኢራን ትናንት ማክሰኞና ከትናንት በስቲያ ረቡዕ «አካሄድኩ» ያለችው የሚሳይል ሙከራ ዩናይትድ ስቴትስንእንዳሳሰባት ግን፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል።
"ጉዳዩን ከመረመርን በኋላ ተስማሚና አስፈላጊ የሆነ ምላሽ በተመድ በኩል ወይም አብረን በጋራ መልስእንሰጥበታለን" ሲሉ፣ የውጩ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አባይ ጆን ኪርቢ ተናግረዋል።