በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአረቢ ራቢጣ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ


የአረቢ ራቢጣ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትላንት በግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ ባደረጉት ስብሰባ ሰሞኑን በሳዑዲ አረቢያና በኢራን መካከል ስላለዉ የፓለቲካ ዉዝግብ ድጋፋቸዉን ለጀዳ አሰምተዋል። ሳዑዲ አረቢያ አንድ የሺያ የሃይማኖት መሪ በሞት ከተጣች በኋላ ኢራን በአጸፋ ኤምባሲዋ ላይ ጥቃት ማድረሰዋን ተከትሎ ስምንት የአረብ አገሮች ከቴህራን ጋር ዲፕሎማሳዊ ግንኙነታቸዉን ማቋረጣቸዉ ተዘግቧል።

የተባበሩት የአረብ ኤምረቶች ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሴክ አብደላ ቤን ዛይድ ኢራን በሂስ ሲጠርቡ በአረብ ራቢጣ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ባሰሙት ንግግር፣ ኢራን በመካከለኛዉ ምስራቅ አካባቢ የበላይነትዋን ለማስፈንና በሌሎች አገሮች የየዉስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የእስልምና ዘርፍ ልዩነትና ትጠቀማለት ብለዋል።

አክለውም፣ የተባበሩት የአረብ ኤምረቶች ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ኢራን ነዉጠኛ ሃይሎችና አሸባሪዎችን ትደግፋለች ታሰለጥናለች ታስጣጥቃለች በዚህም በአካባቢዉ አመጽና ቀዉስን አንግሳለች ብለዋል።

የሳዑዲ አረቢያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አደል ጁቤር (Adel Jubeir)በበኩላቸዉ መንግስታት ላይ አመጽ የሚፈጽሙ ሰላዮትን በአረብ አገሮች ዉስጥ በመመልመልና ኢራንን ከሰዋል። ቴህራን በጎሬቤቶችዋ የዉጭ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንድትቆጠብም ጥሪ አድርገዋል።

ሳዑዲ አረቢያ የሱኒ ሺያ ግጭት አትፈልግም ሆኖም እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር ከ1979 ዓ.ም. አብዮች ወዲህ ኢራን የእምነት ልዩነት እየዘራች ነዉ ሳዑዲ ግን ትቃወማለች ብለዋል።

ሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ የሺያ እስልምና መሪ ሼህ ኒሚር አል ኒሚርን አንግት በመቅላት መግደልዋን ተከትሎ ኢራናዉያን ተቃዋሞዎች ቴህራን ዉስጥ የሚገኘዉን ኤምባሲዋን በማጥቃት በእሳት ያጋዮት። ሆኖም ባለፈዉ ሳምንት ባሰሙት ንግግር የኢራን ፕሬዚደንት ሃሳን ሮሃኒ (Hassan Rouhani) እርምጃዉ ስህተትና ሕገወጥ መሆኑን ተናግረዉ፣ ሳዑዲ አረቢያ ግን የሪያድ ንጉሳዊ አገዛዝ ላይ ሂስ ይሰነዝር የነበረዉ ኒሚር አል ኒሚር በመግደል የፈጸመችዉን ወንጀል ከኢራን ጋር ግንኙነትዋን በማቋረጥ ላይ የፈጸመችዉን ወንጀል ልትሸፋፍነዉ አትችልም ብለዋል።

ኢራን ከጎሬቤቶችዋ ጋር ያለዉን ዉጥረት ለማብረድ ጥብቅ እርምጃ እንትድወስ የአረብ ራቢጣ መሪ ነቢል ኤላራቢም (Nabil Elarabi)በበኩላቸው ጠይቀዋል።

በግራ በኩል የአረብ ራቢጣ ዋና ጸሃፊ ነቢል ኤላራቢም (Nabil Elarabi) የቀጠር ሚኒስተር ሼክ ሃመድ ቢን ጃሲም ቢን ጃብር አል ታሃኒ (መሃል)፣ እና አህመድ ቢን ሄሊ የአረብ ራቢጣ የፖለቲካዊ ጉዳዮች ተባባሪ ጸሃፊ ጀነራል፣ በሶርያ ጉዳይ ላይ ለመወያየት በተሰበሰቡበት ወቀት የተነሳ ፎቶ
በግራ በኩል የአረብ ራቢጣ ዋና ጸሃፊ ነቢል ኤላራቢም (Nabil Elarabi) የቀጠር ሚኒስተር ሼክ ሃመድ ቢን ጃሲም ቢን ጃብር አል ታሃኒ (መሃል)፣ እና አህመድ ቢን ሄሊ የአረብ ራቢጣ የፖለቲካዊ ጉዳዮች ተባባሪ ጸሃፊ ጀነራል፣ በሶርያ ጉዳይ ላይ ለመወያየት በተሰበሰቡበት ወቀት የተነሳ ፎቶ

ኢራን ተጨባጭ የግንኙነት ማሻሻል እርምጃ በመዉሰድ በዉስጥ ጉዳያችን ትገባለች የሚለዉን የጎረቤቶችዋን ስጋት መቀነስ አለባት ነዉ ያሉትነቢል ኤላራቢም (Nabil Elarabi)።

ቤይሩት በሚገኘዉ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሬፌሰር ሂላል ካሻን (Hilal Khashan) ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ሲናገሩ የአረብ ራቢጣ የሚኒስትሮች ጉባኤ ተጨባጭ የመፍትሔ እርምጃ ማስገኘቱ አጠራጣሪ ነዉ ብለዋል።

"ሳዑዲዮች የድጋፍ መግለጫ ነዉ የፈለጉት ፣ አግኝተዋል፥ ሌላ መፍትሔም አልፍለጉም አልጠበቁምም" ብለዋል።

ኢራን ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ያላትን ልዩነት የማባባስ ፍላጎት የላትም ፣ በኤምባሲዋ ላይ በደረሰዉ ጥቃት ምክንያትም ብዙ የቴህራን ጸጥታ ባለስልጣናትን ከስራ አባራለች ብለዋል ሂላል ካሻን (Hilal Khashan)። ስምንት የሚሆኑ የአርብ አገሮች ከኢራን ጋር ወይ ግንኙነታቸዉን አቋርጠዋል ወይም የኤምባሲ ሰራተኞቻቸዉን ቀንሰዋል።

ኤድዋርድ የርኒያን (Edward Yeranian)አጠናቅሮ ያቀረበውን ዝርዝር ትዝታ በላቸዉ አቅርባዋለች ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የአረቢ ራቢጣ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:16 0:00


XS
SM
MD
LG