በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን አራቱን አሜሪካዊያን ለቀቀች


US Iran Flags
US Iran Flags

ኢራን አሥራቸው የቆየች አራት አሜሪካዊያንን መልቀቋን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ አሁን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ “የተያዙ ዜጎቻችንን ወደ ሃገራቸው ለለመመለስ እንዲቻል በተከፈተው የዲፕሎማሲ መሥመር መሠረት ኢራን ውስጥ ተይዘው የነበሩ አራት አሜሪካዊያን መለቀቃቸውን እናረጋግጣለን” ብሏል፡፡

አራቱ አሜሪካዊያን አምር ሄክማቲ፣ ሳየድ አቤዲኒ፣ ጄሰን ሬዛኒያን እና ኖስራቶላ ኾስራቪ-ሩድሳሪ የተለቀቁ ሲሆን ራበርት ሌቪንሰን የሚባለው አሜሪካዊም ያለበትን አስሶ ለማግኘት ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር መተባበሯን እንደምትቀጥል ኢራን አስታውቃለች፡፡

መግለጫው በመቀጠልም “እኛም ለሰባት ኢራናዊያን ምህተት ሰጥተናል” ብሏል፡፡

ስድስቱ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የነበረ ወይም ጥፋተኛነት የተበየነባቸው የአሜሪካና የኢራን ዜግነት ያላቸው መሆናቸውን መግለጫው አመልክቷል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት ኢንተርፖል አማካይነት የፍለጋ ቀይ ማስታወቂያ አውጥታባቸው ከነበሩ 14 ኢራናዊያን ላይም የአደን ዘመቻዋን ማንሣቷን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ በዚሁ መግለጫው አስታውቋል፡፡

እንዲሁም አሥራ አራቱ ኢራናዊያን ባሉበት ተይዘው እንዲሰጧት ዩናይትድ ስቴትስ አውጥታ የነበረው ጥያቄ ቀና ምላሽ የማግኘቱ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡

XS
SM
MD
LG