በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጂቡቲ ከኢራን ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጣለች


የጂቡቲ ካርታ
የጂቡቲ ካርታ

የጂቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በዓለምአቀፍ ትብብር ቃል አቀባይ፣ ኢራን ዓለምአቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ግዴታዎቿን ማክበር ይጠበቅባታል ሲልም መግለጫው አክሏል።

ጂቡቲ ቴህራን በሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ከኢራን ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጣለች።

ጂቡቲ፥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በዓለምአቀፍ ትብብር ቃል አቀባይዋ በኩል ትላንት ባወጣችው መግለጫ፥ የመንግሥቱ ቃል አቀባይ በቴህራንና በማሻድ(Mashhad) የደረሱትን ጥቃቶ በከፍተኛ ደረጃ አውግዟል ብሏል።

ኢራን ዓለምአቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ግዴታዎቿን ማክበር ይጠበቅባታል ሲልም መግለጫው አክሏል።

በተያያዘ ዜና፥ የሱማልያ መንግሥትም ከ 20 ዓመታት የርስ በርስ ጦርነት በማገገም ላይ የምትገኘውን ሀገር ፀጥታ ለማደፍረስ ትሞክራለች ሲል በመክሰስ ከኢራን ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን ማቋረጡን አስታውቋል።

ከውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ትላንት የወጣው መግለጫም፥ ሱማእያ ተጠባባቂ አምባሳደሯን ከኢራን ጠርታለች፥ የኢራን ዲፕሎማቶችም ሱማልያን በ 72 ሰዓት ውስጥ ለቅቀው እንዲወጡ ታዘዋል ይላል።

የኢራን ኤምባሲና ሞቃዲሾ የሚገኘው ኢማም ኮመኒ(Imam Khomeni) የተባለው የረድዔት ድርጅት ከመንግሥቱ እውቅና ውጭ፥ በየጊዜው ገጠሩን እየጎበኙ፥ በየመን፥ ሊባኖስና ኢራቅ እንደሚያደርጉት በሱማልያም ታጣቂ ቡድኖችን ለማቋቋም ሞክረዋል ሲልም መግለጫው አብራርቷል።

የሱማልያ ሠጥታ ኃይሎች ባለፈው ወር ሞቃዲሾ ውስጥ የሺሃ ሙስሊሞችን እምነት ለማስፋፋት የሞከሩ ሁለት ኢራናውያን ይዘው ማሠራቸው ይታወሳል።

ኢራን ክሱን መሠረተ ቢስ ስትል አትቀበልም።

የዜና ዘገባ አለን የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያዳምጡ።

ጂቡቲ ከኢራን ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጣለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:35 0:00

XS
SM
MD
LG