በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራን ፍርድ ቤት ሙስና ፈጽመዋል በተባሉ ግለሰሰቦች ላይ የሞት ፍርድ በየነ


ባለጠጋው ባባክ የታሰረው እ.አ.አ. በ2013 ዓ.ም. ሲሆን፣ የወቅቱ ፕሬዚደንት ሃሰን ሩሃኒ ሥልጣን ላይ እንደመጡና ሙስናን ለማጥፋት በወሰዱት ቀዳሚ አጀንዳ መሠረት ነው።

አንድ የኢራን ፍርድ ቤት፣ ከነዳጅ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ሙስና ፈጽሟል በተባለ አንድ ቢሊዬነር እና በሌሎች ሁለት ግለሰሰቦች ላይ የሞት ፍርድ በየነ።

ኢራን ውስጥ ከፍተኛ ባለጸጋ መሆኑ የሚነገርለት ባባክ ዛንጃኒ ወደ $14 ቢልዮን እንዳለው ተጠቅሷል።

የተከሰሰውም፣ በቀድሞው የኢራን ፕሬዚደንት መሃመድ አህመዲነጃድ መንግሥት ስር በነዳጅ ሽያጭ ከ$2 ቢልዮን በላይ አጭበርብሯል ተብሎ ነው።

ባባክ ዛንጃኒ
ባባክ ዛንጃኒ

ባለጠጋው ባባክ የታሰረው እ.አ.አ. በ2013 ዓ.ም. ሲሆን፣ የወቅቱ ፕሬዚደንት ሃሰን ሩሃኒ ሥልጣን ላይ እንደመጡና ሙስናን ለማጥፋት በወሰዱት ቀዳሚ አጀንዳ መሠረት ነውም ተብሏል። የተቀሩት ሁለቱ ተከሳሾች ይግባኝ ለማለት እንደሚችሉ ተገልጧል።

XS
SM
MD
LG