በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጋምቤላ ውስጥ መቶ አርባ ሰው ተገደለ


የጋምቤላ ክልልን የሚያሳይ ካርታ /ጉግል ማፕ/
የጋምቤላ ክልልን የሚያሳይ ካርታ /ጉግል ማፕ/

ድንበር ተሻግረው ጥቃቱን ያደረሱት የመሪሌ ጎሣ አባላት ናቸው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ከስሷል። ከመቶ በላይ ሕፃናት ተጠልፈው ተወስደዋል።

ደቡብ ሱዳንን በሚያዋስነው የኢትዮጵያ ምዕራባዊ ድንበር አካባቢ ታጣቂዎች 140 ሰዎችን መግደላቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።

ድንበር ተሻጋሪ ጥቃቱ ጋምቤላ ውስጥ የደረው በመሪሌ ጎሣ ታጣቂዎች ዓርብ፤ ሚያዝያ 7/2007 ዓ.ም. እንደሆነ የመንግሥቱ መግለጫ አመልክቷል።

ጋምቤላ ከተገደሉት ሰዎች መካከል ሴቶችና ህፃናት እንደሚገኙበትና ሌሎችም ታግተው ወደ ደቡብ ሱዳን መወሰዳቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ለአሶሼትድ ፕሬስ የዜና ምንጭ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ /ፋይል ፎቶ - ሮይተርስ/
የኢትዮጵያ መንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ /ፋይል ፎቶ - ሮይተርስ/

የመሪሌ ጎሣ ታጣቂዎች ከደቡብ ሱዳን ድንበር የተሻገሩ መሆኑን የገለፁት የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ጥቃቱን ያደረሱት ታጣቂዎች ከደቡብ ሱዳን መንግሥትም ሆነ አማፂያኑ ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ስድሣ የሚሆኑ አጥቂዎችን መግደላቸውን የገለፁት አቶ ጌታቸው ወደ ደቡብ ሱዳን ተሻግረውም አጥቂዎቹን ሊያሳድዱ እንደሚችሉም አስረድተዋል።

ዛሬ ማምሻውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በቴሌቭዥን ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ መንግሥታቸው በደረሰው ጥቃት ማዘኑን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ /ፋይል ፎቶ/
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ /ፋይል ፎቶ/

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጋምቤላ ውስጥ 140 ሰው ተገደለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG