በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጋምቤላ ግጭቶች ውስጥ ሰነበተች


ጋምቤላ ካርታ
ጋምቤላ ካርታ

ጋምቤላ ክልል ውስጥ ሰሞኑን እየተፈጠሩ ባሉ ግጭቶች ብዙ ህይወት መጥፋቱ እየተዘገበ ነው።

ጋምቤላ ክልል ውስጥ ሰሞኑን እየተፈጠሩ ባሉ ግጭቶች ብዙ ህይወት መጥፋቱ እየተዘገበ ነው።

በጋምቤላ ከተማ እንዲሁም በኒለንና በኦሚንኛ ሠፈሮች፣ ስደተኞች በተጠለሉባቸው ኢታንግ እና ፑኝዶ አካባቢዎች ሁሉ በክልሉ አኝዋክና ኙወር ብሄረሰቦች አባላት መካከል ዛሬን ጨምሮ እየተካሄድ መሆናቸው ተዘግቧል።

አንዳንድ ዘገባዎች ሰሞኑን የተገደለው ሰው ቁጥር ሃያ መድረሱን ቢዘግቡም የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪ ባለፉ ሁለት ወራት ብልጭ ድርግም በሚሉ ግጭቶች እስከ ሃምሣ ሰው የሚደርስ ሕይወት መጥፋቱን ይናገራሉ፡፡ በጥቃትና በበቀል እርምጃዎች የክልሉን የገጠር መንገዶች ሥራ ቢሮ ምክትል ኃላፊን ጨምሮ የብዙ ሰው ሕይወት ጠፍቷል።

የጋምቤላ የፀጥታ ኃላፊ አቶ ፒተር ሪክሪክ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ሁኔታውን በቁጥጥር ሥር ያዋሉ መሆናቸውን፣ እያጣሩ እንዳሉና ጋምቤላ ወደ ተረጋጋ ሕይወቷ መመለሷን ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጋምቤላ ግጭቶች ውስጥ ሰነበተች
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:02 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG