በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የጋምቤላ ማህበረሰብ አባላት እንዲፈቱ የመብት ድርጅቶች ጥሪ አቀረቡ


ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የዓለም ባንክ በጋምቤላ ክልል ባካሄደው የውስጥ አሰራር ምርመራ ጥናት በአስተርጓሚነት ያገለገሉት ግለሰብና ሁለት ሌሎች የቀረበባቸው የሽብር ክስ እንዲሰረዝ የመብት ድርጅቶች ጠየቁ።

የዓለም ባንክ በጋምቤላ ክልል ባካሄደው የውስጥ አሰራር ምርመራ ጥናት በአስተርጓሚነት ያገለገሉት ግለሰብና ሁለት ሌሎች የቀረበባቸው የሽብር ክስ እንዲሰረዝ የመብት ድርጅቶች ጠየቁ።

ሒውማን ራይትስ ወችና ስድስት የዓለም አቀፍ ልማትና መብት ድርጅቶች እንደሚሉት ከሆነ ሶስቱ ግለሰቦች የታሰሩት በናይሮቢ በሚካሄድ ዓለም አቀፍ የምግብ ዋስትና ጉባዔ ተሳትፎ ጋር በተያያዘ ነው

በዚህ ባሳለፍንው ዓመት የመጨረሻ ሳምንት ነበር ቄስ ኦሞት አግዋ፣ አሺኔ አስቲን፣ እና ጀማል ኡመር ሆጄሌ ክስ የተመሰረተባቸው። ሶስቱ ግለሰቦች ለ6ወራት ይህል ክስ ሳይመሰረትባቸው በቁጥጥር ስር የቆዩ መሆናቸውን ሂውማን ራይትስ ወች ገልጿል።

“የክሱን ዝርዝር ከተመለከትን ከሽብር ጋር የሚያገናኘው ጉዳይ የለም።” ብለዋል ፊሊክስ ሆርስ የሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ቀንድ መረጃ አጠናቃሪ።

“የተከሰሱት በምግብ ዋስትናና የመሬት ይዞታ ዙሪያ በተሰናዳ ጉባኤ ላይ በናይሮቢ በመሳተፋቸው ነው”

በነዚህ ግለሰቦች ላይ የቀረበው ክስ፤ በመሰረቱ የኢትዮጵያ መንግስት ከልማትና ሌሎች አስተዳድራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከዜጎቹ መስማት የማይፈልገውን ድምጽ ሲያሰሙ ስለማይወድ ነው ይላሉ።

“የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ያለውን አሰራር በአግባቡ እንዲያጤን፤ በተለይ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማህበረሰቡ ለማድረስ የዘረጋቸው መርሃ ግብሮች ለሰብዓዊ መብት ጥሰት ውለው ከሆነ፤ ለማጣራት ባደረገው ምርመራ በአስተርጓሚነት ተካፍለዋል።”

ትውልዳቸው ጋምቤላ አካባቢ የሆነው አቶ ኦባንግ ሜቶ የጋር እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የተባለ የማሀበረሰብ ተቋም ይመራሉ። አቶ ኦሞት አጓ የመካነየሱስ ቄስና የተከበሩ ሰው ናቸው ይላሉ’

ሂውማን ራይትስ ወች ለኢትዮጵያ መንግስት አጭር መልእክት አስተላልፏል። “ክሱ በፍጥነት ውድቅ መሆን አለበት” የሚል

የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ ከሂውማን ራይትስ ወች የሚቀርቡ የመብት ጥሰት ትችቶችን፤ ቡድኑ ተዓማኒነት የለውም በማለት ውድቅ ያደርጋል።

የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የጋምቤላ ማህበረሰብ አባላት እንዲፈቱ የመብት ድርጅቶች ጥሪ አቀረቡ 2’48”
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG