በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዝነኛው ኢትዮጵያዊ የረዥም ርቀት ሩጫ አሰልጣኝ ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ አረፉ


አሰልጣኝ ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ /ፋይል ፎቶ/
አሰልጣኝ ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ /ፋይል ፎቶ/

አትሊት ስለሺ ስህንና አትሊት ኃይሌ ገብረሥላሴም፥ “የሩጫ ብቻ ሳይሆን የመልካም ሥነ ምግባር አስተማሪና አባት” ሲሉ በጠሯቸው በዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት በእጅጉ ማዘናቸውን ገልጸዋል።

ዋና አሰልጣኝ ወልደመስቀል ኮስትሬ ለከፍተኛ ስኬት ካበቋቸው አትሌቶች መካከል ኃይሌ ገብረሥላሴ፥ ቀነኒሳ በቀለ፥ ጥሩነሽ ዲባባና ደራርቱ ቱሉ ይጠቀሳሉ። ዓለምአቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር IAAF ወዲያውኑ ባወጣው መግለጫ፥ ”ለረዥም ጊዜ ታመው የቆዩትን አሰልጣኝ በማጣታችን ጥልቅ ሃዘን ይሰማናል። ለቤተሰቦቻቸውና በጠቅላላው ለአትሌቶቹ መጽናናቱን እንመኛለን” ብሏል።

አትሊት ስለሺ ስህንና አትሊት ኃይሌ ገብረሥላሴም፥ “የሩጫ ብቻ ሳይሆን የመልካም ሥነ ምግባር አስተማሪና አባት” ሲሉ በጠሯቸው በዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት በእጅጉ ማዘናቸውን ገልጸዋል። ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ የስፖርት ሳይንስ የተማሩት ሁንጋሪያ ውስጥ መሆኑ ሲታወቅ፥ በዛሬው ዕለትም በኢትዮጵያ የሁንጋሪያ አምባሳደር ባሰልጣኙ መሞት ማዘናቸውን ገልጸዋል።

በሌላ ዜና፥ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብ ውስጥ በመካከለኛ ርቀት በ 800 ሜትር ተወዳዳሪ የነበረችውና፥ በብሔራዊ ቡድን ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ተመራጭ በመሆን የምትታወቀው የ 19 ዓመቷ አትሌት ኩለኒ ገልቻ፥ ከወንድ ጓደኛዋ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በአትሌት ጓደኛዋ እጅ ህይወቷ በስለት ማለፉን፥ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብን በምንጭነት ጠቅሶ ለአሜሪካ ድምጽ ገለጿል።

ዝነኛው ኢትዮጵያዊ የረዥም ርቀት ሩጫ አሰልጣኝ ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ አረፉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:23 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG