በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍቅሩ ኪዳኔ ለስፓርት እድገት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ተሸለሙ


አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ለስፓርት እድገት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ሽልማት እየተቀበሉ
አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ለስፓርት እድገት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ሽልማት እየተቀበሉ

ማኅበሩ አቶ ፍቅሩን የሸለመው፥ ለአህጉሪቱ የስፖርት እና ፕሬስ እድገት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽፆ መሆኑን በመግለጫው አመልክቷል።

የአልጄሪያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር፥ በአፍሪካ ስፖርት የዳበረ ልምድ ላላቸውና ባሁኑ ወቅት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት የኢሳ ሃያቱ (Issa Hayatou) ልዩ አማካሪ ለሆኑት ኢትዮጵያዊ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ፥ የክብር ሽልማት በዚህ ሳምንት ሰጥቷል።

ማህበሩ አቶ ፍቅሩን የሸለመው፥ ለአህጉሪቱ የስፖርት እና ፕሬስ እድገት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽፆ መሆኑን በመግለጫው አመልክቷል።

የአልጄሪያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር፥ የዓለምአቀፉ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር የአፍሪካ ፕሬዘዳንት ሚሼል ቢ(Michel bi)ም፥ በአህጉር ደረጃ የአፍሪካን ስፖርት ደረጃ ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል ሲል ሽልማቱን ሰጥቷል።

አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ
አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ

የሽልማቱ ሥነ ሥርዓት ትላንት የተካሄደው፥ አልጀርስ ውስጥ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሰኞ በተካሄደው የአፍሪካ ጋዜጠኞች የሥነ ምግባር ሴሚናር ጎን መሆኑ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG