በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ውስጥ 2 ወጣቶች ለማምለጥ ሲሞክሩ ሞተዋል፣ 11 ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተባለ


የኤርትራ ማስታወቅያ ሚኒስቴር አቶ የማነ ገብረ መስቀል እ.አ.አ. 2016 /ፋይል ፎቶ/
የኤርትራ ማስታወቅያ ሚኒስቴር አቶ የማነ ገብረ መስቀል እ.አ.አ. 2016 /ፋይል ፎቶ/

የተለያዩ የኤርትራውያን ተቃዋሚዎች ሬድዮዎችና ድረ-ገጾች ግን የሞቱት ወጣቶች ብዛት ከአራት እስከ 11 ነው ይላሉ።

አስመራ ውስጥ ሁለት በብሄራዊ አገልግሎት ላይ የነበሩ ወጣቶች ባለፈው እሁድ ከተጫኑባቸው መኪኖች ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ በደረሰባቸው ጉዳት ሞተዋል ሲሉ የኤርትራ ማስታወቅያ ሚኒስቴር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገልጸዋል።

ሌሎች ከመኪኖቹ ዘለው ለማምለጥ የሞከሩ 11 ወጣቶች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል ብለዋል።

ፖሊሶች ጥቂት ጥይቶች ወደ ሰማይ በመተኩስ እንዲረጋጉ አድርገዋል ሲሉም አቶ የማነ አክለዋል።

የኤርትራ መዲና አስማራ ከተማ /ፋይል ፎቶ/
የኤርትራ መዲና አስማራ ከተማ /ፋይል ፎቶ/

የተለያዩ የኤርትራውያን ተቃዋሚዎች ሬድዮዎችና ድረ-ገጾች ግን የሞቱት ወጣቶች ብዛት ከአራት እስከ 11 ነው ይላሉ።

የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ከኤርትራ ባለስልጣኖች ምላሽ ለማግኘ ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካለትም።

የኤርትራ መዲና አስማራ ከተማ /ፋይል ፎቶ/
የኤርትራ መዲና አስማራ ከተማ /ፋይል ፎቶ/

ኤርትራ ውስጥ ያለው ገደብ አለባ ብሄራዊ አገልግሎት ወጣቶች አደገኛ ጉዞም ባለበት መንገድ ከሀገር እንዲሰደዱ ምክኒያት እንደሆነ ስለ ኤርትራ የሰብአዊ መብት አያያዝ እንዲያጣራ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተመሰረተው አካልና የተለያዩ የሰብአዊ መብት ቡድኖች ይነቅፋሉ።

XS
SM
MD
LG