በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ ባለፈው እሁድ ተኩስ እንደነበር ታውቋል


ፋይል ፎቶ - የኤርትራ ወታደሮች በአስመራ ከተማ እ.አ.አ. 2007
ፋይል ፎቶ - የኤርትራ ወታደሮች በአስመራ ከተማ እ.አ.አ. 2007

በወታደራዊ ስልጠና ላይ የነበሩ ወጣቶች በወታደራዊ መኪኖች ተጭነው ያልፉ በነበረበት ወቅት አንዳንዶቹ ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ እንደከፈቱባቸው ምንጮች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጠቁመዋል።

በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ ባለፈው እሁድ ተኩስ እንደነበር ታውቋል። በወታደራዊ ስልጠና ላይ የነበሩ ወጣቶች በወታደራዊ መኪኖች ተጭነው ያልፉ በነበረበት ወቅት አንዳንዶቹ ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ እንደከፈቱባቸው ምንጮች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጠቁመዋል።

የኤርትራ መዲና አስማራ ከተማ /ፋይል ፎቶ/
የኤርትራ መዲና አስማራ ከተማ /ፋይል ፎቶ/

በተኩሱና ተያይዘው በደረሱ ጉዳቶች የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች እንዳሉ በተለያዩ የተቃዋሚዎች ሚድያ እየተገለጸ ነው። የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ስለሞቱትም ሆነ ስለቆሰሉት ሰዎች በነጻ ምንጭ ማረጋገጥ አልቻለም።

ስለ ጉዳዩ ከኤርትራ ባለስልጣኖች ምላሽም ለማግኘት ሞክረን አልተሳካልንም።

ፋይል ፎቶ - ወጣቶች በወታደራዊ መኪኖች ተጭነው እ.አ.አ. 2000
ፋይል ፎቶ - ወጣቶች በወታደራዊ መኪኖች ተጭነው እ.አ.አ. 2000

XS
SM
MD
LG