በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኤርትራ የለውጥ ድባብ እያንዣበበ ነው ይላሉ የመደረክ አስተባባሪ ዶክተር አሰፋው ተኸስተ

የኤርትራ ካርታ
የኤርትራ ካርታ

የኤርትራውያንን ስጋት መሰረት በማድረግ ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ያላት ስትራቴጂ ምን እንደሆነ ለመረዳት የመድረኩ ተወካዮች አዲስ አበባ ድረስ ተጉዘው ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና ከሌሎችም ባለስልጣኖች ጋር እንደተነጋገሩ ገልጸዋል።

የሀገራዊ ውይይት መድረክ በሚል የተመሰረተው የተበታተኑ ኤርትራውያን ተቃዋሚ ሃይሎችን በማሰባሰብ በሀገሪቱ ለውጥ ለማምጣት በመጣር ላይ ያለው መደረክ አስተባባሪ ዶክተር አሰፋው ተኸስተ በኤርትራ የለውጥ ድባብ እያንዣበበ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የኤርትራውያንን ስጋት መሰረት በማድረግ ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ያላት ስትራቴጂ ምን እንደሆነ ለመረዳት የመድረኩ ተወካዮች አዲስ አበባ ድረስ ተጉዘው ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና ከሌሎችም ባለስልጣኖች ጋር እንደተነጋገሩ ገልጸዋል።

የኤርትራ ካርታ
የኤርትራ ካርታ

ዶክተር አሰፋው ተኸስተ ከአንጋፍ የኤርትራ የህዝባዊ ግንባር ታጋዮች አንዱ የነበሩ። መጀመርያ ላይ ለፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደብዳቤ ከጻፉት 13 ሰዎችም እንዱ እንደነበሩ ገልጸውልናል።

በትግሉ ወቅት በህክምና ክፍል ያገለግሉ እንደበር ኤርትራ ራስዋን የቻለች ሀገር ከሆነች በኋላ ለአጭር ጊዜ በማኅበራዊ ጉዳዮች ሃላፊ ሆነው እንደሰሩ ከዚያም በአስመራ ዩኒቨርሲት ዲን እንደነበሩ፣ እዚህ ዩናይትድ ስቴስ መጥተው ደግሞ ትምህርት በመቀጠል ካሊፎርኒያ በሚገኘው ቶሮ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ጤና ጥበቃ ፕሮፌሰር ሆነው እንደሚሰሩ ጠቁመዋል። ዶክተር አሰፋውን ያነጋገረችው አዳነች ፍሰሀየ ናት። ቃለ-ምልልሱን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

በኤርትራ የለውጥ ድባብ እያንዣበበ ነው ይላሉ የመደረክ አስተባባሪ ዶክተር አሰፋው ተኸስተ
please wait

No media source currently available

0:00 0:22:47 0:00

XS
SM
MD
LG