በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዞን9 የኢተርኔት ዓምደኞች ጉዳይ ሌላ ቀጠሮ ሰጠ


ዞን-9
ዞን-9

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የአሸባሪነት ክስ የቀረበባቸዉ የኢንቴርነት አምደኞች ጉዳይ ላይ ለመወሰን ዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ዉሳኔዉ አልደረሰልኝም በማለት ነዉ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮዉን የሰጠዉ።

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በአቃቤ ሕግና በነሶሊያና ሽመልስ መዝገብ የአሸባሪነት ክስ የቀረበባቸዉ የኢንቴርነት አምደኞች ጉዳይ ላይ ለመወሰን ዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ዉሳኔዉ አልደረሰልኝም በማለት ነዉ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮዉን የሰጠዉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የዞን 9 የኢተርኔት ዓምደኞች ማለትም ብሎገሮች ከእስር ከተፈቱ ከ5 ወራት በኋላ፣ የኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ዳግም እየተፈነ ነው፣ ምክያቱም እነዚህ ብሎገሮች በነፃነት የመንቀሳቀስ ዕድላቸው የተገደበ መሆኑን ይናገራሉ።

ከእስር ቤት መልስ፣ የጋዜጠኛነት ሕይወት ምን እንደሚመስልና ይልቁንም ይህ አሁን በእነርሱ ዙሪያ እየተከሰተ ያለው ሁኔታ በእነርሱ በጋዜጠኝነት ሙያ ላይ ምን አንደምታ ይኖረዋል? መለስካቸዉ አመሃ የፍርድ ቤቱን ዉሎ፥ ተከታትሏል።

ኢትዮጵያውያን የድረ-ገጽ ዓምደኞች ወቅታዊ ሁኔታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:42 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኢትዮጵያውያን የድረ-ገጽ ዓምደኞች ወቅታዊ ሁኔታ

የሃያ-ዘጠኝ ዓመቱ አቤል ዋቤላ፣ ከሌሎች 8 ብሎገሮችና ፍሪ-ላንሶች ጋር የአንድ ዓመት ተኩል የእስር ቤት ሕይወት አሳልፏል። አቤል ከእስር ከተለቀቀ 5 ወራት ቢያልፈውም ታዲያ፣ ሕይወት ግን ለእርሱ ቀላል አልሆነለትም። አቤል ቀደም ሲል አየር መንገድ ውስጥ የቴክኒክ መሓንዲስ ነበር። አሁን ግን ወደ ቀደመ ስራው አይመልሱትም።

የታሠሩት ብሎገሮች /የፎቶ ምንጭ - ECADF ዌብሳይት/
የታሠሩት ብሎገሮች /የፎቶ ምንጭ - ECADF ዌብሳይት/

እራሱ እንደገለጸው፣ እስር ቤት ውስጥ በደረሰበት እንግልት የተነሳ፣ ግራ ጆሮው በትክክል አይሰማም። ብሎገሮቹ ፓስፖርቶቻቸውን የተነጠቁ ሲሆን፣ የተከሰሱትም፣ በኢትዮጵያው የፀረ-ሽብርተኛነት ህግ መሠረት፣ ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን በመጠቀም አገሪቱ ውስጥ አመጽ እንዲነሳ ቀስቅሳችኋል ተብለው ነው። "ምንም እንኳ ከ5 ወራት በፊት ከእስር ብለቀቅም" ይላል ሌላው፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ "ዛሬም ግን በፍርሃት ነው የምኖረው።" ብሏል።

ፋይል ፎቶ - ኢትዮጲያውያን ጋዜጠኞች በናይሮቢ ኬንያ እአአ 2006 ጋዜጠኞች ነፃ እንዲወጡ ጥሪ እያቀረቡ
ፋይል ፎቶ - ኢትዮጲያውያን ጋዜጠኞች በናይሮቢ ኬንያ እአአ 2006 ጋዜጠኞች ነፃ እንዲወጡ ጥሪ እያቀረቡ

"ከእስር ብለቀቅም ቅሉ፣ ክትትል እየተደረገብኝ ስለሆነ የትም አልንቀሳቀስም። ተመልሼ እንዳልታሰርም እፈራለሁ። እራሱ ዐቃቤ-ህጉ ይግባኝ ማለቱ፣ ዛሬም እጄ በሰንሰለት የታሰረ ያህል ነው የሚሰማኝ። እናም እራሴን ለእስር ቤት እያዘጋጀሁ ነኝ።" ብሏል

ለሰብዓዊ መብት መከበር የቆሙ ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያን የፕሬስ ነፃነት አያያዝ ደጋግመው ይተቻሉ። መንግሥት ደግሞ፣ ሁሌም፣ "እነዚህ እኔ የማስራቸው ሰዎች፣ በጋዜተኛነት ሽፋን የሚንቀሳቀሱ ወንጀለኞች ናቸው" ነው የሚለው። ኬሪ ፓተርሰን (Kerry Paterson) ዋና ጽ/ቤቱ ኒው-ዮርክ የሆነውና ለጋዜተኞች መብት መከበር በቆመው ሲቲጄ (CPJ) ውስጥ፣ የአፍሪቃ ተመራማሪ ናቸው።

እነዚህ ዓምደኞች ወደ እስር ቤት እንደሚመለሱ የሚያመለክተው አዝማሚያ ተቀባይነት የሌለውና በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ላይም ከፍተኛ አደጋ የሚደቅን ነው ይላሉ።

የፕሬስ ነፃነትን በተመለከተ እነዚህ የድረ-ገጽ ዓምደኞች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖራቸው የወደፊት ሁኔታ ብሩህ ሆኖ ባይታያቸውም አቤል፣ አጥናፍና ሌሎቹም ዓምደኞች፣ ዛሬም በተለያዩ ድረ-ገጾች መዘገባቸውን ግን አላቆሙም።

ማርተ ቫን ደር ውልፍ ከኢንተርኔት አምደኞቹ ጥቂቶቹን አነጋግራ ከአዲስ አበባ የላከችውን ዘገባ አዲሱ አበበ አጠናቅሮታል። የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዞን9 የኢተርኔት ዓምደኞች ጉዳይ ሌላ ቀጠሮ ሰጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:09 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG