ከአፍሪካ ህብረት ጋር በጋራ የሚሰራው All Africa Music Awards በምህፃረ ቃል “AFRIMA” አመታዊ የሽልማት ዝግጅት ቅዳሜ ህዳር 15 2011 በጋና ኣክራ በግዙፉ ብሄራዊ አዳራሽ ለአምስተኛ ጊዜ ተካሂዷል። የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ቱሪዝም ሚኒስትር፣ ዲፕሎማቶች፣ በርካታ የጥበብ ሰዎችና አለም አቀፍ ሚዲያዎችን ጨምሮ አምስት ሺህ ተጋባዞች በምሽቱ ታድመው ነበር።
ትውልደ-ሶማሌዪቱ ኢላን ኦማር እና ከኮሎራዶ አንድ ጥቁር አሜሪካዊ ለኮንግረስ ሲመረጥ የመጀመሪያ የሆኑት የኤርትራ-አሜሪካዊያን ልጅ ጆዜፍ ንጉሤ የዩናይትድ ስቴትስ እንደራሴዎች ሆነው ተመርጠዋል።
ዛሬ በመላ ዩናይትድ ስቴትስ የአማካይ ዘመን ምርጫ እየተካሄደ ነው።
የሸገር 102.1 የለዛ የሬድዮ ፕሮግራም አመታዊ ሽልማት ከሁለት ቀናት በፊት ለስምንተኛ ጊዜ ተካሄዷል ።
ከ60 ዓመት በላይ ባህላዊ የኦሮምኛ ድምፃዊና የማሲንቆ ሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች የነበሩት ለገሰ አብዲ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። ስርዓተ ቀብራቸው በትላንትናው ዕለት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል። ለአድናቂዎቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን!
በቡራዩና አካባቢዋ በደረሰው ጥቃት የተፈናቀሉ ዜጎች በአዲስ አበባ በተለያዩ ትምህርት ቤቶችና የወጣት ማዕከሎች ውስጥ መጠለላቸው ይታወቃል። የሚገኙበትን ሁኔታ ጠይቀናቸው ነበር።
በቡራዩና አካባቢዋ በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ከ 17 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች በ8 የተለያዩ ጊዜያዊ መጠለያዎች በመረዳት ላይ ይገኛሉ። ተፈናቃዮቹ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?
ኬንያ የህፃናትን ሞት ቁጥር ለመቀነስ የእናት ጡት ወተት ማጠራቀሚያ ባንክ ልትጀምር ነው። የናት ጡት ወተት ለሚያስፈልጋቸው ህፃናት ከማንኛዋም እመጫት እናት በፈቃደኝነት የተለገሰን ወተት በማሰባሰብና በማስቀመጥ ከአፍሪካ ሁለተኛዋ ሃገርም ለመሆን ዝግጅቷን ጨርሳለች።
በሊቢያ የእርስ በእርስ ጦርነት እየተባባሰ በመምጣቱና ያለጠባቂ በመተዋቸው ምክንያት ግንብ ንደው ከመጠለያው እንዳመለጡ 30 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለቪኦኤ ገለፁ። ከጦርነት ቀጠና ሸሽተው አሁን ያሉበት ቢደርሱም በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በፍጥነት ወደ ሃገራችን እንዲመልሰን እንማፀናለንም ብለዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ስደተኞቹን ወደ ሃገር ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ገልፀዋል።
አዲስ አበባ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኢምባሲ አዘጋጅነት ለአንድ ወር የተዘጋጀው የበጎ ፈቃድ የዕውቀት ልውውጥ ትላንት ተጠናቀቀ። የእውቀት ልውውጡ አሜሪካን ስፔስስ የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም በምህፃረ ቃል ASVP ይባላል።
በጣልያን ተቀባይነት ሳያገኙ ሜዲትራኒያን ባህር በነፍስ አድን መርከብ ላይ ለአንድ ሳምንት የቆዩ 150 አፍሪካውያን ስደተኞች ከሁለት ቀናት በፊት ጣልያንለመግባት በቅተዋል። በተመሳሳይ ከሁለት ወራት በፊት ከሊቢያ በአነስተኛ ጀልባ ተጉዘው ጣልያን ወደብ የደረሱ ሌሎች 150 ገደማ የሚገመቱ አፍሪካውያን ስደተኞች ወደ መጡበት ሊቢያ በጣልያን የነፍስ አድን መርከብ እንዲመለሱ ተደርጎ ነበር። ከተመላሾቹ መካከል ጥቂቶቹን ሴት ስደተኞች አነጋግረናል።
በተለያዩ የአለማችን ሃገራት በዚህ በያዝነው የበጋ ወራት ከዚህ ቀደም ከነበረው በተለየ ከፍተኛ የሙቀት ሞገድ ተመዝግቧል። ቀድሞ ከ35 ዲግሪ ሴልሽይስ የማይበልጥ የሙቀት መጠን ይታይባቸው በነበሩ ቦታዎች ዘንድሮ 40 ሴልሽየስ የሙቀት መጠን ተመዝግቧል። በቅርቡ በአየር ንብረት ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚያመላክተው በአለማችን እየታየ ያለው ከፍተኛ የሙቀት ሞገድ በሚቀጥሉት ቅርብ አመታትም በተደጋጋሚ ሊከሰት እንደሚችል አመላክቷል።
በአለማችን በሚሊየኖች የምትወደደው የሶል ሙዚቃ ንግስቷ ኣሪታ ፍራንክሊን በ76 ዓመትዋ ዛሬ ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች። ለረጅም ጊዜ በህመም ስትሰቃይ የነበረችው አሜሪካዊቷ ድምፃዊት በዩናይትድ ስቴትስ ከመጀመሪያ ረድፍ ከተቀመጡት አንጋፋ የጥበብ ሰዎች ቀዳሚዋ ነበረች።
ሊቢያ በሚገኘው አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ዩ ኤን ኤ ች ሲ አር (UNHCR) የስደተኞች መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በከፍተኛ ረሃብ፣ በሽታና ህመም ላይ እንደሚገኙ ለቪኦኤ ገልፀዋል። ሊቢያውያኑ የጥበቃ ሰራተኞች ከስደተኞቹም የተወሰኑትን እየተለቀሙ እየወሰዱ እንደሆነና የሄዱበትንን ማንም እንደማያውቅ ጨምረው ገልፀዋል። ለደህንነታችን እንሰጋለን፣ ለባርነት ጠባቂዎቹ አሳልፈው እንደማይሸጡን ምንም ዋስትና የለንም ይላሉ።
በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝት በተመለከተ የሰጡት አስተያየት።
ባሳለፍነው እሁድ የኢትዮጵያንና የኤርትራን የሰላም ማብሰሪያ ዝግጅት ላይ ለመታደም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኝተው ነበር። በሚሊኒየም አዳራሽ የሁለቱም ሃገራት መሪዎች የተገኙበትን ዝግጅት ለማድመቅ ወደ አራት መቶ የሚጠጉ የጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተውም ነበር።በመድረኩ ከተጋበዙት ድምፃውያን መካከል ቴዎድሮስ ካሳሁንና ሃጫሉ ሁንዴሳ ያስተላለፉት መልዕክት ተከትሎ በርካታ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን አስተያየቶች ተሰጥተዋል። የተፈጠርው ምን ነበር? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ።
ባሳለፍነው ወር 'ፍለጋ' በሚል ስያሜ ለሶስት ቀናት የአዝማሪዎች ዜማ ለተመልካች ቀርቦ ነበር። እየሳሳ የሚገኘውን የአዝማሪነት ሙያ ለመታደግ በዩኔስኮ የገንዘብ እርዳታ ነበር የተዘጋጀው። ከትግራይ ፣ከአማራና ከኦሮሚያ ክልሎች የተሰባሰቡት እነዚህ አዝማሪዎች አጭር ሙያዊ ስልጠና ከቀድሞ የሙያ አጋሮቻቸው እንዲያገኙም እንደተደረገ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።
በዚህ ዓመት ብቻ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች ወደ ደቡባዊ የአውሮፓ ሀገራት ለመድረስ የሜዲትራኒያንን ባህር አቋርጠዋል። ጣልያንና ማልታ በየባህር ወደቦቻቸው የደረሱ ስደተኞችን አንቀበልም በማለታቸው ምክንያት በርካታ ስደተኞች ሜዲትራኒያን ባህር ላይ ህይወታቸውን እያጡ ነው። ሜዲትራኒያንን ባቋረጡ በርካታ ስደተኞች በሚጠሩዋቸው ቅፅል ስም "የስደተኛ አባት" አባ ሙሴ ዘርዓይ አጀንሲያ ሀበሻ የተሰኘ የምግባረ ሰናይ ድርጅት መስራችና ስራ አስኪያጅ ናቸው።
ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን በሁለቱ ሃገሮች መካከል የተጀመረው የሰላም ጉዞና በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድና በፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተፈረሙ ስምምነቶች እንዳበረታትዋቸውና ተስፋ እንደሰጧቸው እየገለፁ ነው። ከኢትዮጵያም ከኤርትራም ነዋሪዎችን አነጋግረናል።
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በዚህ ሳምንት ከስነ-ጥበብ ባለሙያዎች ጋር ያደረጉት ውይይት ሁሉን ያካተተ አልነበረም ሲሉ አንዳንድ የመድረክ ሰዎች ተናገሩ። በአንጻሩ በስብሰባው የተሳተፉ ባለሙያዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ የስነጥበብ ሰዎች ለማህበረሰብ ብልጽግና፣ ለፈጠራ ስራ መስፋፋትና መጎልበት የሚኖራቸውና ሊኖራቸው ይገባዋል ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ገለጻ ማድረጋቸውንና ጠቃሚ ሆኖ እንዳገኙት እየተናገሩ ነው።
ተጨማሪ ይጫኑ