በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮፓ አሜሪካ ዛሬ ማታ ዩናይትድ ስቴትስና ኮሎምቢያ ካሊፎርንያ ውስጥ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል

የኮፓ አሜሪካ አርማ
የኮፓ አሜሪካ አርማ

16 ቲሞች የሚፋለሙበት ይህ ዓለምአቀፍ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሲደረግ ለመደመሪያ ጊዜ ይሆናል።

አንጋፋው የአሜሪካዎቹና ካሪቢያን አህጉራዊ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ማለት ኮፓ አሜሪካ (COPA America)ዛሬ ማታ ዩናይትድ ስቴትስና ኮሎምቢያ ሳንታ ክላራ ካሊፎርንያ (Santa Clara, California) በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል።

16 ቲሞች የሚፋለሙበት ይህ ዓለምአቀፍ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሲደረግ ለመደመሪያ ጊዜ ይሆናል።

ኮፓ (COPA America)የተጀመረበትን 100ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ዛሬ በሚጀመረው ጨዋታ፥ ጉዳት ደርሶባቸው ከቀሩ በጣት ከሚቆጠሩ የዓለም ዝነኛ ተጫዋቾች አብዛኞቹ ይገኛሉ ተብሏል።

በቲም ደረጃም ባለፈው የዓለም ዋንጫ ለሩብ ፍጻሜው ከደረሱ ስምንቱ መካከል አራቱ ይሳተፋሉ። የስፖርት ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ ሰሎሞን ክፍሌ ይህ ታላቅ ውድድር ከመጀመሩ በፊት ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ኮፓ አሜሪካ ዛሬ ማታ ዩናይትድ ስቴትስና ኮሎምቢያ ካሊፎርንያ ውስጥ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:07 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG