በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቦትስዋና ለ10 የኤርትራ ተጫዋቾች ጥገኝነት ፈቅዳለች


የኤርትራ እግር ኳስ ተጫዋች
የኤርትራ እግር ኳስ ተጫዋች

ቦትስዋና በቅርቡ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ማጣርያ ግጥሚያቸውን ካደረጉ በውኃላ በሃገሯ ከለላ ለጠየቁት 10 የኤርትራ ተጫዋቾች የጥገኝነት መብት መፍቀዷን ጠበቃቸው ዛሬ አስታወቁ።

ቦትስዋና በቅርቡ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ማጣርያ ግጥሚያ ለመሳተፍ የሄዱትን 10 የኤርትራ እግር ኳስ ተጫዋቾች ጥገኝነት ፈቅዳለች። ስፖርተኞቹ ጥቅምት 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቦትስዋና ቡድን ጋር ከተጫወቱ በውኃላ ነው ወደ ሃገራቸው በሚወስዳቸው አውሮፕላን ላይ አንሳፈርም ብለው ከለላ የጠየቁት።

“የቦትስዋና መንግሥትን እናመሰግናለን። የተደረሰው ውሳኔ የሚያሳየውም በቦትስዋና ሕግና ሥርዓት እንደሚከበርና የፍትሕ ሂደቱም እንደሚሠራ ነው” ሲሉ በፕሪቶሪያ “የኤትራ የዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች እንቅስቃሴ” አባል የሆኑት የስፖርተኞቹ ጠበቃ አቶ እያሱ ሐብተማርያም ተናግረዋል።

እንቅስቃሴው ለሕጋዊ አገልግሎት ክፍያ የሚውል ገንዘበም ያሰበስባል።

​የኤርትራ እግር ኳስ ተጫዋች

የኤርትራ እግር ኳስ ተጫዋቾች ከዚህ ቀደምም፣ እአአ በ 2009 በኬንያ በ 2011 በታንዛንያ በ 2012 በዩጋንዳ መቅረታቸው ተነግሯል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለአንድ ዓመት ምርመራ ካካሄደ በውኃላ፣ በኤርትራ እንደ ባርነት የሚቆጠር አያያዝና ሰቆቃ በስፋት ይዘወተራል ብሏል። የዓለሙ ድርጅት ምርመራ በተጨማሪም፣ ኤርትራ ዜጎቿን ላልተወሰነ ግዜ በሚቆይ የብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት ታሠማራለች ለማምለጥ የሚሞክሩትንም ገድላለች ይላል።

የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ለቀረቡት ክሶች በትክክል ለየትኛው መሁኑን ሳያመለክት የዓለሙን ድርጅት ሪፖርት ባጠቃላይ ውድቅ አድርጓል።

ቦትስዋና ለ10 የኤርትራ ተጫዋቾች ጥገኝነት ፈቅዳለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:30 0:00

XS
SM
MD
LG