በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

30ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር


please wait

No media source currently available

0:00 0:04:36 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


30ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር በ Equatorial Gunea በይፋ ከተጀመረ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ፥ በአራት ምድብ ተከፍለው ለፍጻሜው ግጥሚያ ከሚፋለሙት 16 ብሄራዊ ቲሞች 14ቱ የመጀመሪያ ዙር ግጥሚያቸውን አድርገዋል። የቀሪዎቹ ሁለቱ ማለት የ Mali እና Cameroon ከአንድ ሰዓት በሗላ ይካሄዳል።

አሁን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባበቃው Ivory Coast እና Gunea ባደረጉት ጨዋታ፥ አንድ ተጫዋቹን በቀይ ካርድ አጥቶ በጎደሎ የተጫወተው የአይቮሪኮስት ቡድን አቻ ያደረገችውን ጎል በ 72ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሮ በእኩል 1 ለ 1 ተለያይቷል።

አድማጮች ዛሬ ተሳክቶልኝ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔን Malabo ከተማ አግኝቼአቸዋለሁ። በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ብዛት ያላቸው፥ ለአውሮፓ ፕሪምየር ሊግ የሚጫወቱ ከዋክብት መገኘታቸው ከቀደምቱ ሁሉ እንደለየው ይነግሩናል። በኢኳቶሪያል ጊኒ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የሥራ መስኮች ተሠማርተው እንዳሉም ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG