በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ስለፊፋ ፕሬዚዳንት ይናገራሉ


A bulldozer pulls part of a statue of king Ramses II found at the Matariya area, north of Cairo, Egypt, March 13, 2017.
A bulldozer pulls part of a statue of king Ramses II found at the Matariya area, north of Cairo, Egypt, March 13, 2017.

ሴፕ ብላተር ለአምስተኛ ጉዜ በተመረጡበት ጉባዔ ላይ የተሣተፉት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ጁኔይዲ ባሻ ቲልሞ ለብላተር እንደገና መመረጥ የድጋፍ ድምፅ ከሰጡት የብሄራዊ ፌዴሬሽኖች መሪዎች መካከል ናቸው፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:42 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ዓለምአቀፉ የእግርኳስ ማኅበራት ፌዴሬሽን /ፊፋ/ ውስጥ የተፈጠረው ቀውስ እና የፕሬዚዳንቱ ሴፕ ብላተር ከኃላፊነት ለመልቀቅ መወሰን እግር ኳስ ተወዳጅ የውድድር ስፖርት በሆነባት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ትኩረት ስቧል፡፡

“አፍሪካ በብላተር አመራር ያገኘችው ጥቅም በገንዘብ የሚቆጠር በዐይንም የሚታይ ነው” ያሉት ሴፕ ብላተር ለአምስተኛ ጊዜ በተመረጡበት ጉባዔ ላይ የተሣተፉት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ጁኔይዲ ባሻ ቲልሞ ምሣሌ ሲጠቅሱ ፊፋ ለኢትዮጵያ በዓመት የሚሰጠው የድጋፍ ክፍያ ከ250 ሺህ ዶላር ወደ 750 ሺህ ዶላር ማደጉን ገልፀዋል፡፡

ሴፕ ብላተር ከኃላፊነት ለመልቀቅ የደረሱበት ውሣኔ የተጠበቀ እንዳልነበረም አቶ ጁነይዲ አመልክተዋል፡፡

ለዝርዝሩ ከአቶ እስክንድር ፍሬው ከአቶ ጁነይዲ ባሻ ጋር ያደረገውን ቃለ-ምልልስ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG