በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሴካፋ ዋንጫ ተፋላሚዎች ተለዩ


የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ሻምፒዮና ሊጠናቀቅ ነው።

ኢትዮጵያ በምታስተናግደው 38ኛው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ሻምፒዮና፥ የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያዎች ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂደዋል።

በቅድሚያ የተጫወቱት ሩዋንዳና ሱዳን ሲሆኑ በመደበኛውና በተጨማሪው ሰዓት ባለመሸናነፋቸው አሸናፊው የተለየው በመለያ ምት ነው። በዚሁ መሠረት ሩዋንዳ 4 ለ 2 በሆነ ውጤት ለፍጻሜው አልፏል።

ቀጥለው የተጫወቱት ኢትዮጵያና ዩጋንዳም መተመሳሳይ አሸናፊው የተለየው በመለያ ምት ሆኗል። ዩጋንዳ 4 ለ 3 አሸንፋ ለዋንጫ ፍጻሜ አልፋለች።

ኢትዮጵያና ሱዳን የፊታችን እሁድ ለደረጃ ይጫወታሉ። ዜናውን ከዚህ በታች ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የሴካፋ ዋንጫ ተፋላሚዎች ተለዩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:58 0:00

XS
SM
MD
LG