በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አስቀድመው የHIV ቫይረስ መከላከያ የሚወስዱ ሰዎች ቫይረሱን የማስተላለፍ እድላቸው ይቀንሳል


"ኤድስን በ15 ዓመታት ጊዜ ማጥፋት" የWHO ግብ
"ኤድስን በ15 ዓመታት ጊዜ ማጥፋት" የWHO ግብ

ታካሚዎች የሰውነት መከላከያ እንክብል (ARV) የሚሰጣቸው የበሽታ መከላከያ ቁጥር ከተወሰነ ድረጃ በታች ሲወርድ ነው። በአዲሱ አሰራር በቫይረሱ መያዛቸው የታወቀ ሰዎች በፍጥነት የመከላከያ ህክምና ያስፈልጋቸዋል።

የዓለም የጤና ድርጅት ረቡእለት ይፋ ባደረገው የህክምና ጥናት መሰረት ኤድስን በሚያመጣው HIV ቫይረስ የተያዙ ሰዎች አስቀድመው የሰውነት መከላከያ መድሃኒቱን (ART) ከወሰዱ ረጂምና ጤናማ ህይወት ይኖራቸውል።

የህክምና ጥናቱ እንደሚያመለክተው የHIV መከላከያ እንክብሉን በሽታው ሳይበረታ ያገኙ ታማሚዎች ለጾታ ግንኙነት ጓዶቻቸው ቫይረሱን የማስተላለፍ እድላቸው ይቀንሳል።

የHIV ቫይረስ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ሁሉ የሰውነት መከላከያ መድሃኒት በፍጥነት ማግኘት አለባቸው ብሏል የዓለም የጤና ድርጅት። ይህንን ለመተግበር የሚያስችል መርህም በዛሬውለት አውጥቷል።

ከዚህ ቀደም የነበረው የዓለም የጤና ድርጅት አሰራር ታካሚዎች የሰውነት መከላከያ እንክብሉ የሚሰጣቸው የሰውነታቸው የመከላከያ ነጭ ደም ሴል ቁጥር ከተወሰነ ድረጃ በታች ሲወርድ ነው። WHO እንደሚለው በቫይረሱ መያዛቸው የታወቀ ሰዎች በፍጥነት የመከላከያ ህክምና ያስፈልጋቸዋል።

በአሁኑ ወቅት ካሉት የሰውነት መከላከያ እንክብሉን የሚወስዱት ሰዎች ቁጥር 28 ሚሊዮን ሲሆን፤ በዚህ አዲስ የአሰራር መመሪያ መሰረት በዓለም ዙሪያ በHIV/AIDS የተያዙት 37 ሚሊዮን ሰዎችን ያካትታል።

​የአፍሪካ የኤችአይቪ/ኤድስ ሥርጭት
​የአፍሪካ የኤችአይቪ/ኤድስ ሥርጭት

አስቀድሞ መጠንቀቅ

የኤድስ ታማሚዎችን የህክምና አገልግሎት ለማድረስ ጥረቶች መጠናከራቸውን የገለጸው የዓለም የጤና ድርጅት፤ በሽታውን በመከላከል ያተኮሩ ስራዎች መጠናከር እንደሚገባቸው ጨምሮ አሳስቧል።

የማህበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫና ሌሎች መርሃግብሮችም የመከላከል ስራዎቻቸውን በሁለት ወንድ ፍቅረኞች መካከል ብቻ ሳይወስኑ፤ በስፋት በማህበረሰቡ ውስጥ ሊሰሩ ይገባቸዋል ብሏል።

ኤድስን በ15 ዓመታት ጊዜ ማጥፋት

የተባበሩት መንግስታት የጤና ድርጅት ባወጣቸው አዳዲስ ግቦች ያካተተው ሌላ ነጥብ የኤድስን ወረርሽን በ2022 ዓ.ም. ከምድር ማጥፋት ነው።

ይሄን ግብ ለማሳካት በHIV ቫይረስ የተያዙት ውስጥ 90 ከመቶው ተመርምረው እራሳቸውን ማወቅ ይገባቸውል፤ የሰውነት መከላከያ መድሃኒቶችንም ሊያገኙ ይገባቸዋል። ዘጠና ከመቶው ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ሰዎች የበሽታው ተውሳክ በደማቸው እንዳይታይ የማድረግ እቅድም ወጥቷል።

እቅዱ ከተገበረ የ21 ሚሊዮን ሰዎችን ህይወት የሚያተርፍ ሲሆን፤ በሚቀጥሉት 15 ዓመታት 28 ሚሊዮን ሰዎችን በበሽታው እንዳይያዙ ይረዳል።

XS
SM
MD
LG