ዋሽንግተን ዲሲ —
የዓለም የጤና ድርጅት ዛሬ ታስቦ በዋለው የኤችአይቪ/ኤድስን (HIV/AIDS) ቀን ጫና የሰጠበት ነጥብ ከኤችአይቪ/ኤድስ (HIV/AIDS) ጋር ለሚኖሩት ሰዎች ሁሉ የሚሰጠው የአንታይ-ሬትሮቫይራል ህክምና መስፋፋት አለበት የሚል ነው።
በዓለም ደረጃ የኤችአይቪ/ኤድስን (HIV/AIDS) ካለባቸው 37 ሚልዮን ሰዎች መድሀኒቱን የሚያገኙት 16 ሚልዮን ብቻ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅቱ የጤና አገልግሎት ገልጾ የኤችአይቪ/ኤድስን (HIV/AIDS) ወረርሽን ለማጥፋት የሚቻለው ሁሉም መድሀኒቱን እንዲያገኙ በማድረግ እንደሆን አስገንዝቧል።
ቫይረሱ እንደያዛቸው ወድያውኑ ህክምናውን የጀመሩ ሰዎች ጤናቸው ከመጠበቅ አልፎ ለሌሎች ማስተላለፉም ሊቀንስ እንደሚችል ጥናቶች ማመልከታቸውን ጠቁሟል።
የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ካሮል ፒርሰን (Carol Pearson) ያጠናቀረችውን ዘገባ ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።