የቀይ መስቀል ማህበር በጋምቢያ፣ በሞሪታንያ፣ በማላዊ፣ በናሚብያ፣ በሴኔጋልና በዚምባብዌ ያሉትን ከ 200,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ለመርዳት የ $8 ሚልዮን ዶላር የአስቸኳይ እርዳታ ለማግኘት ዘመቻ ጀምሯል።
ሰዎቹ አንድ አይነት የአየር ሁኔታ ካስከተው ቀውስ ሳያገግሙ ሌላ አይነት ቀውስ ስለሚገጥማቸው ከምግብ እጥረት አዙሪት ለመውጣት ከባድ ሆናባቸዋል ሲሉ አለም አቀፍ የቀይ መቀል ፌደርሽን ቃል አቀባይ Benoit Carpentier ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ተናግረዋል።
“በየአመቱ መልሰው የሚገነቡት ነገር በየአመቱ እያሽቆለቆለ ነው። የረድኤት ጥሪ ያቀረብነው እንዲህ አይነቱን ችገር ለመቋቛም ነው። ችግሩ ጊዜ አይሰጠንም” ሲሉ Carpentier አስገንዝበዋል።
ቤተሰቦች በረሃብ ምክንየት ልጆቻቸውን ከትምህርት ቤት አስወጥተው በስራ ላይ እንዲሰማሩ ሊያደርጉ ይችላሉ። ሴቶች ደግሞ ምግብ ለማግኘት ሲሉ በወሲብ ተግባር በመግባት ለ HIV ሊጋለጡ ይችላሉ በማለት አለም አቀፍ የቀይ መቀል ፌደርሽን ቃል አቀባይ Benoit Carpentier አስረድተዋ።