በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዘመቻ “ዜሮ”ን ማሣካት ቢታሰብም የበጀት እጥረት ሥጋት አለ


ዜሮ ኤድስ
ዜሮ ኤድስ

የዘንድሮው የዓለም የኤድስ ቀን የታሰበውና ፀረ-ኤድስ እንቅስቃሴዎቹም የሚካሄዱት “ዜሮ ማግለል፣ ዜሮ በኤችአይቪ መያዝ፣ ዜሮ የኤድስ ሞት” በሚል መርኅ ነው፡፡



please wait

No media source currently available

0:00 0:10:18 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የአፍሪካ የኤችአይቪ/ኤድስ ሥርጭት ገፅታ
የአፍሪካ የኤችአይቪ/ኤድስ ሥርጭት ገፅታ

ይህ በመጭዎቹ ሃያ አምስት ወራት ውስጥ፣ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር እስከ 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ መጨበጥ ይቻላል ተብሎ የተቀመጠ ግብ ነው፡፡ “ይቻላል?” … ዛሬ በመላው ዓለም ከአንድ ሺህ በላይ ሕፃናት ከኤችአይቪ ጋር ይወለዳሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት ሁለተኛ ዓመት የልደት ቀናቸውን አያዩም፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ፀረ-ኤችአይቪ/ኤድስ እንቅስቃሴው እየተከናወነ ስላለበት ሁኔታ ተደርሶበታል ስለተባው ደረጃ ባለፈው ቅዳሜ ታስቦ ከዋለው የዓለም የኤድስ ቀን ጋር ተያይዞ ውይይት ጀምረናል፡፡
ግሎባል ፈንድ በየደቂቃው ሁለት ሺህ ሕይወት ከሞት ያተርፋል፤ ግሎባል ፈንድ በየደቂቃው ሁለት ሺህ ሕይወት ከሞት ያተርፋል፤ በጉልህ ለማየት ምሥሉን ይጫኑት፤ ይበልጥ ለማጉላት እንደገና ይጫኑት
ግሎባል ፈንድ በየደቂቃው ሁለት ሺህ ሕይወት ከሞት ያተርፋል፤ ግሎባል ፈንድ በየደቂቃው ሁለት ሺህ ሕይወት ከሞት ያተርፋል፤ በጉልህ ለማየት ምሥሉን ይጫኑት፤ ይበልጥ ለማጉላት እንደገና ይጫኑት

አቶ ዓለሙ አኖ፣ በኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት የዘርፈ-ብዙ ምላሽ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር፤ አቶ ደረጀ ዓለማየሁ፣ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሰዎች ማኅበራትና መረቦች መረብ ዋና ዳይሬክተር፤ አቶ መንግሥቱ ዘመነ፣ የአንጋፋውና በኢትዮጵያ ከግዙፎቹ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሰዎች ማኅበራት አንዱ የሆነው የመቅድም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ዶ/ር አጎናፍር ተካልኝ፣ ለኤችአይቪ/ኤድስ የሚሰጠው ምላሽ ቀዳሚ ተሣታፊ፣ መሪና ተሟጋች፣ እንዲሁም አሁን የኢትዮጵያ የወባ መከላከያና መቆጣጠሪያ ኮንሰርቲየም ዋና ዳይሬክተር ናቸው የውይይቱ ተሣታፊዎች፡፡

በዛሬው የውይይቱ የመጨረሻ ክፍል የሚነሣው የበጀትና የገንዘብ አጠቃቀም ጉዳይ ነው፡፡ ለመሆኑ - አቅም ሊያጥረን ይችላል፤ ምንጭ ሊደርቅ ይችላል የሚል ሥጋት አላችሁ? ተብለው ሲጠየቁ “አለ” ይላሉ፡፡

የውይይቱን የመጨረሻ ክፍል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG