በርካታ የኢትዮጵያ የጥበብ ባለሙያዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በቤተመንግስት ተገናኙ።
ዓለም አቀፉ በቤት ውስጥ ስራ የተሰማሩ ሰዎች ቀንን በማስመልከት የእግር ጉዞና ሰላማዊ ሰልፍ በቤሩት ተካሄደ። በቤሩት ለስራ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በመገኘት ችግሮቻችን ይፈቱ፣ ድምፃችንን ይሰማ ሲሉ መፈክሮቻቸውን አሰምተዋል።
የብሩክታይት ጌታሁን በመድረክ ቅፅል ስሟ የቤቲ ጂ ሁለተኛ አልበም ዛሬ ገበያ ላይ ውሏል። በዛሬው ምሽት የ'ወገግታ' አልበም የቤቲ ጂ አድናቂዎችና የሙያ አጋሮች በተገኙበት ተመርቋል።
አለም አቀፉን የስደተኞች ቀን ለማክበር ቀናቶች ሲቀሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰደተኞች በስፔን የባህር ወደብ ከተማ ደርሰዋል። በሶስት ጀልባዎች የተሳፈሩ 600 ስደተኞች የስፔኗ ቫለንቲካ ወደብ ከትላንት በስትያ ደርሰዋል። የደቡብ አውሮፓ ሀገራት ወደ ባህር ወደቦቻቸው የሚፈልሱ ቁጥራቸው የበዛ ስደተኞችን በተመለከተ መፍትሔ ለማበጀት ጥሪ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
የተባበሩት መንግስታት የደህንነት ምክር ቤት በየመን የሁዴዳን ከተማን ፀጥታ በተመለከተ ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠዋል። በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው የአረብ አገሮች ጣምራ ጦር በሁቲ አማፅያን ቁጥጥር ስር በሆነችው የየመን ዋና የባህር በር ሁዴዳ ላይ ጥቃት በማድረስ ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታትና ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት የከተማዋ ነዋሪዎችና በሃገሪቱ በሚልየን የሚቆጠሩት ዜጎች ለረሃብና ለተለያዩ በሽታዎች እንድሚጋለጡ ተናገሩ።
በዩናይትድ ስቴይትስ ብዙ ሰዎችን ከሚያስተናግዱ የአውሮፕላን ማረፊያዎች አንዱ በሆነው ኦ-ሄይር አየር ማረፊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚያደርገው በረራ በዩናይትድ ስቴይትስና ኢትዮጵያ መካከል የንግድና የምጣኔ ሀብት ትስስርን የሚያጠናክር እንደሚሆን ተገልጿል።
ትላንት ማምሻውን ከቱኒሲያ የባህር ወደብ አምስት ማይል ርቀት እንደተጓዘ ነው 180 ፍልሰተኞችን የጫነው ጀልባ የሰመጠው። እስከአሁን በጀልባዋ ተሳፍረው ከነበሩት ውስጥ 68ቱ ከሞት ተርፈዋል። 60 ፍልሰተኞች አስክሬን ተገኝቷል። የተቀሩት 52 ስደተኞችን ማፈላለጉ ቀጥሏል።
በዩናይትድ ስቴትስ ኢምባሲ አማካኝነት ለሶስት ቀናት ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተዘጋጅቶ ነበር።
በዩናይትድ ስቴትስ ከዩኒቨርስቲዎችና ከኮሌጆች በኮምፕዩተር ሳይንስ ሙያ ከሚመረቁት ተማሪዎች መካከል ሴቶች 18 በመቶ ያነሱ ናቸው። አዳጊ ሴቶች በመስኩ እንዲበለፅጉ ግፊት ያስፈልጋል።
ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት WHO ህጻናት ከተወለዱ ሁለት አመት እስኪሆናቸው ድረስ የእናት ጡት ቢመገቡ ከ820 ሺህ በላይ የሚሆኑ ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህጻናትን ጤንነት መታደግ ይቻላል ሲል አስታውቋል።
የማሊው ስደተኛ ማማዱ ጌሳማ ከአራተኛ ፎቅ ለመውደቅ የተንጠለጠለ የ4 አመት ህፃንን በሚያስገርም ፍጥነት ወደ ህንፃው ተንጠላሎ በመውጣትአድኗል። ከትላንት ጀምሮ ይህ በጎ ምግባሩ በአለም ዙሪያ በቴሌቭዥንና ሬድዮ ዘገባዎች እንዲሁም በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን በሰፊው እየተሰራጨ ነው።የፈረንሳዩ መሪ ኢማኑኤል ማርኮን ማማዱ ጌሳማ ለፈፀመው ጀብዱ የፈረንሳይ ዜግነትነት ሰጥተውታል። የቪኦኤ የባምባራ ዝግጅት ክፍል ወጣቱን አነጋግሮት ነበር፤ወደ አማርኛ መልሰን አቅርበንላችኃል።
በ79 ዓመቷ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው ኤርትራዊቷ ታጋይና አንጋፋ ድምፃዊት ፀሐይቱ በራኺ ለአመታት ትኖርበት በነበረው ኒዘላንድስ የሙዚቃ አድናቂዎቿ በተገኙበት የፀሎትና የስንብት ስነስርዓት ትላንት ተካሄደ። ስርዓተ ቀብሯም በነገው እለት በኤርትራ ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በሳዑዲ ያደረጉትን ጉብኝት በማስመልከት በሃገሪቱ የሚኖሩ የኢትዮጵያ የማህበረሰብ መሪዎች የተሰጡት አስተያየት።
በሆሊዉድ ፊልሞች ላይ የመተወን ህልሟ እስኪሳካ በሆሊዉድ አውራጎዳናዎች ላይ እውቅ የፊልም ገፀባህሪያትን አልባሳት ተላብሳ ከጎብኚዎች ጋር ፎቶግራፍ በመነሳት በምታገኘው ሽርፍራፊ ገንዘብ ኑሮዋን በመግፋት ላይ ትገኛለች።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለረመዳን በሰላም አደረሳችሁ!
ማክሰኞ ምሽት የተካሄደው አመታዊው የኢትዮጵያ የፊልም ሽልማት "ጉማ ሽልማት" በተለያዩ የፊልም ዘርፎች ብቃታቸውን ላሳዩ ኢትዮጵያዊ የፊልም ባለሙያዎች ሽልማት ሰጥቷል።
አመታዊው አለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል (Filmfest DC) ከ45 የተለያዩ ሀገራት የተገኙ 80 ፊልሞችን ለአስራ አንድ ተከታታይ ቀናት ለእይታ በማቅረብ የተመሰረተበትን 32 ኛውን ዓመት ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ አክብሯል።
ድምፃዊ ታምራት ደስታ ከአመታት በፊት ስለራሱ ከተናገረው በጥቂቱ የተወሰደ። ለቤተሰቦቹና ለሙያ አጋሮቹ መፅናናትን እንመኛለን!
ኤርትራውያንና ሱዳናውያን ስደተኞችን በሚመለከት የእስራኤል መንግስት ያወጣውን ህግ በመቃወም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞችና የእስራኤል ዜጎች በጋራ ተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፎችን አካሂደዋል። ጩኸታችን የተወሰነ ለውጥ አስገኝቶልናል፤ መፍትሔ እስከምናገኝም እንቀጥላለን በማለት ከስደተኞቹ አንዱ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በቅርቡ ስደተኞችን የተመለከተ የሰጡትን የተስፋ ቃል ከሰዓታት በኃላ አጥፈው አስብበታለው ማለታቸው በርካታ ስደተኞችን አሳዝኗል።
ሴትና ወንድ አዳጊ ልጆችን አፍኖ በመጥለፍ አሳልፎ በገንዘብ የመግዛትና የመሸጥ ወንጀል በዩናይትድ ስቴትስ በእጅጉ በመበራከት ላይ ይገኛል። ሀገር አቀፍ የህገወጥ የፆታ ንግድን የሚከታተለው ድርጅት በዘረጋው የስልክ መስመር ቢያንስ 20 አዳዲስ መረጃዎችን በየቀኑ ይመዘግባል። ሜሪላንድ ግዛት የሚገኘው የምርመራ ፖሊስ አፋኞቹና ህገወጥ ድርጊት ፈፃሚዎቹን ለመያዝ ከመስራት ይልቅ አዳጊ ልጆቹን የማዳን ስራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል።
ተጨማሪ ይጫኑ