በዓለም ዙሪያ፣ ከግጭቶች እና ከሌሎችም ስጋቶቻቸው ከለላ ፍለጋ፣ አገራቸውን ጥለው ለወጡ ከ35 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች መፍትሔ ይፈለግላቸው ዘንድ፣ የመንግሥታቱ ድርጅት ባለሥልጣናት ተማጥኖ አቅርበዋል።
ከሶማሊላንድ የመጡትና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሰፍረው የነበሩ ስደተኞች፣ ደኅንነታቸው የበለጠ ወደሚጠበቅበት ቦታ ተወስደው በመስፈር ላይ እንደኾኑ፣ የተመድ የስደተኞች ተወካይ አስታወቀ። ሊሳ ሽላይን ከጄኔቫ ያጠናቀረችው ዘገባ ነው።
የኮሎምቢያ ህጻናት መብት ተሟጋች ሜዬርሊን ቬርጋራ ፕሬዝ፣ የዚህን ዓመት የናንሰንን የስደተኞች የላቀ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ሽልማቱ የተሰጣቸው ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናትን ከህገወጥ የሰዎች ዝውውርና ከወሲብ ብዝበዛ ጥቃት ተካልክለው በማዳን፣ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነው፡፡
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክኒያት በገቢያቸው ላይ ተፅዕኖ ያሳደረባቸው በአፍሪካ ቀንድና በታላላቅ ሐይቆች አካባቢ ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ስደተኞች ተስፋ ወደ መቁረጥ እያመሩ እንደሆኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር) ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።