በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሕጻናትን ከብዝበዛ የታደጉት ሴት የናንሰንን ሽልማት አሸነፉ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ

የኮሎምቢያ ህጻናት መብት ተሟጋች ሜዬርሊን ቬርጋራ ፕሬዝ፣ የዚህን ዓመት የናንሰንን የስደተኞች የላቀ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ሽልማቱ የተሰጣቸው ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናትን ከህገወጥ የሰዎች ዝውውርና ከወሲብ ብዝበዛ ጥቃት ተካልክለው በማዳን፣ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነው፡፡

የሰብዓዊነት ሽልማቱ፣ በግዳጅ የተፈናቀሉ ሰዎችን በመታደግ አስደናቂ ሥራ ላከናወኑ ሰዎች፣ በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ተቋም፣ በየዓመቱ የሚሰጥ ሽልማት መሆኑም ተነግሯል፡፡

ሜዬርሊን ቬርጋራ ፕሬዝ፣ ማዬ ተብለው ይጠራሉ፡፡ በካሪቢያን ክልል፣ በህጻናትና አዋቂዎች ላይ የሚደረገውን የወሲብ ብዝበዛ ለማስቀረት የሚሠራው፣ ሬናሰር ፋውንዴሽን የተባለው በጎ አድራጎት ድርጅት፣ አስተባባሪ ናቸው፡፡ ድርጅቱ የተቋቋመው ከ30 ዓመት በፊት ሲሆን፣ እስካሁን 22ሺ የሚደርሱ ህጻናትና አዋቂዎችን አድኗል፡፡ “ሬናሰር” የሚለው ቃል በአካባቢው “ዳግመኛ መወለድ” እንደማለት ነው፡፡ የተባበሩት መንግሥታ የስደተኞች ኮሚሽነር ቃል አቀባይ፣ ቦሪስ ቼ ሽ ሮ ኮ ቭ እንደሚሉት፣ ማዬ ቨርጋራ የሰሩት ሥራ፣ ከጀግንነት የተናነሰ ነገር አይደለም፡፡ ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት፣ የማዬ ቫርጋራ ቡድን፣ ህወገጦቹ የሰዎች አዘዋዋሪዎችና ኮንትሮባዲንሶቶቹ፣ በሚዘዋወሩበት አካባቢ ድረስ ዘልቀው የገቡ ቡድኖችን በመምራት መስራታቸውን ገልጸው፣ ይህን ብለዋል፣

ህጻናቱን ፈልገውና ለየተው ያገኟቸዋል፡፡ ከእነዚህ አስከፊ ብዝበዛዎችና አሰቃቂ ሁኔታዎችም ረድተው ያወጧቸዋል፡፡ ልጆቹን ከነዚህ ወንጀለኛ ድርጅቶች እጅ ፈልቅቀው በማውጣት፣ የወደፊት ተስፋ እንዲኖራቸው ለማድረግ ጥረት በሚያደርጉበት ጊዜ፣ የራሳቸውን ህይወት ለአደጋ አጋልጠው በመስጠት መሆኑም ይታወቃል፡፡

ህጻናቱ አንዴ ከአዘዋዋሪዎቹ እጅ እንዲወጡ ከተደረጉ በኋላ፣ ከደረሰባቸው የአእምሮና የስሜት ስብራት እንዲያገግሙ፣ የስነልቦና ምክርና እርዳታ ይሰጣቸዋል፡፡ ከህጉም እርዳታ በተጨማሪ የቀለም ትምህርት የሙያ ስልጠና እየተሰጣቸው አገግመው የሚታነጹበት የ18 ወራት ጊዜ ይኖራቸዋል፡፡ ባለፉት አምስጥ ዓመታት፣ 1.7 ሚሊዮን የሚሆኑ የቬንዝዌላ ስደተኞችና ተፈናቃዮች፣ ወደ የተሻለና ደህንነቱ የተጠበቀ ሥራ ለማግኘት፣ ወደ ኮሎምቢያ ተሰደዋል፡፡ ቼሽሮኮቭ እንዳሉት ከእነዚህ ብዙዎቹ፣ በህግወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች፣ የወንጀል ቡድኖችና ታጣቂዎች እጅ እየወደቁ ተይዘዋል፡፡ በዚህ የተነሳ፣ ለወሲብ ብዝበዛና ንግድ የተጋለጡ፣ ሴቶችና ልጃገረዶች ቁጥር፣ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል፡፡

በዚህ ዓመት ያየነው ነገር ቢኖር ሁኔታው በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በጣም የተባባሰ መሆኑን ነው፡፡ አካባቢያቸውን እየተገደዱ ለሚለቁ ሰዎች ይህ ጊዜ ጥሩ አይደለም፡፡ የበለጠ አስከፊ ነው፡፡ ህጻናትን ከእንዲህ ያለው አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ እንዲወጡ ለመርዳት ማዬ እና ድርጅታቸው የሚሠሩትን ዓይነት ከፍተኛ ሥራ ይጠቃል፡፡

የናንሰን ሽልማት፣ በኖርዌይ እና ስዊስ መንግሥታት፣ ከሚለገሰው ከ150ሺ ዶላር ጥሬ ገንዘብ ጋር የሚሰጥ ነው፡፡ ተሸላሚዎቹ ሎሬቶች፣ የሚያገኙትን ገንዘብ፣ ለሽልማት ያበቋቸውን በጎ ሥራዎች፣ የበለጠ ተግተው እንዲያከናውኑበት፣ ታሳቢ ተደርጎ የተሰጠ፣ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ቀሪውን በድምጽ ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ

ህጻናትን ከብዝበዛ የታደጉት ሴት የናንሰንን ሽልማት አሸነፉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:10 0:00


XS
SM
MD
LG