ግንቦት 21 / 1909 ዓ.ም በዩናይትድ ስቴትስ ምሥራቃዊ ግዛት አንድ "ጃክ" እያሉ የሚጠሩት ኮከብ ተወለደ፡፡ በነፍስ ገዳይ ጥይት በ46 ዓመት ዕድሜው እስከተቀጨ ድረስም በዚህች ምድር ላይ ኖሮ እነሆ እስከዛሬ በዓለሙ ሁሉ እያስተጋባ የሚዘከር፣ የሚነገር ስም ሆነ - ጃን ፊትዠራልድ ኬኔዲ፡፡
የፀረ አበረታች መድሃኒት ቢሮ ስፖርተኞች አበረታች ዕፅ መውሰድ አለመውሰዳቸውን መቆጣጠር መጀመሩንና ከ350 የሚበልጡ አትሌቶች ላይ ምርመራ ማድረጉን አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በጣሊያኗ ሲቺሊ በሚካሄደው የቡድን ሰባት ሀገሮች ስብሰባ ላይ እንዲገኙ መጋበዛቸው "የኢትዮጵያ ቦታና ሚዛን ከፍተኛ ደረጃ እያገኘ መሄዱን ያሳያል" ሲሉ ልዩ መልዕክተኛቸው አስታወቁ፡፡
አፍሪካ ዛሬ ዕድሜያቸው በአብዛኛው ከ35 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች የሚበዙባት አህጉር ነች፡፡ ይሔ ጥቅምም ጉዳትም አለው ይላሉ ጠበብት፡፡ የዘንድሮው የአፍሪካ ቀን ሲታሰብ ወጣቱን በመዋዕለ ንዋይ ማሳተፍና ማስታጠቅ ቀዳሚ አላማ ሊሆን ግድ ይላል፡፡
አዲሱ ተመራጭ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም፤ የጤና ጥበቃ ሥራቸው ለሁሉም ሰው የሚዳረስ የሰብዓዊ መብት እንዲሆን የመሥራት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል።
የሥራ ዘመናቸውን አጠናቀው ሥልጣን የሚለቁት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ማርጋሪት ቻን፣ የዘንድሮውን የድርጅቱን ጉባዔ የከፈቱት አሁን አሁን ድርጅቱ፣ ዋጋውን እያጣ ነው የሚሉትን ሰዎች ትችት ጠንከር ባላ ኃይለ ቃል በማስተባበል ነው፡፡ ማርግሪት ቻን ለአለፉት አሥር ዓመታት የዓለም ጤና ድርጅትን በዳይሬክተርነት ካገለገሉ በኋላ ሥልጣን ሊለቁ ሲሆን ነገ ማክሰኞ ለሚመረጥ ይህን ለዓለም ጤና ጥበቃ ዋና ቁልፍ የሆኑ ድርጅት ለሚመራ ሰው ሥልጣኑን ሊያስረክቡ ነው፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሳውዲ ዓረብያ ውስጥ ባደረጉት በሰፊው ሲጠበቅ የቆየ ንግግራቸው ሙስሊም መሪዎች ፅንፈኝነትን ጨርሶ እንዲደመስሱ ተማፃኑ።
ሰሜን ኮሪያ ትላንት ያካሄደችውን የቦሊስቲክ ሚሳይል ሙከራን ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ አወገዙ።
የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምቀፍ ሃይማኖት ነፃነት ኮሚሽን 16 አሥራ ስድሥት ሀገሮችን አሳሳቢ ሁኔታ ያለባቸው በሚል ፈርጇል። የሁለቱም የሀገሪቱ ፓርቲዎች ትብብርን ያቀፈው የአሜርካ መንግሥት ኮሚሽን በዓለም ዙርያ የሀይማኖት ነፃነት ጉዳይ ስለሚገኝበት ሁኔት ይመዘግባል። ለሀገሪቱ መንግሥት፣ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ለምክር ቤት ምክረ ሃሳብ ያቀርባል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና ሬሴፕ ታይፕ ኤርዶዋን ትናንት ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ውስጥ ያደረጉት ስብሰባ "በሁለቱ ሃገሮች መካከል ለሚኖሩት ግንኙነቶች የአዲስ ዘመን መጀመሪያ ነው" ሲሉ ገልፀውታል፡፡
በአንድ የሶማሊያ ክልል በድርቅ የተነሣ ግማሽ ሚሊዩን ሕዝብ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሏል፣ ሀገሪቱ የችጋር አፋፍ ላይ ነች - ተብሏል፡፡ በተለይ የአልሸባብ አሸባሪዎች በተቆጣጠሩት ደቡባዊ ሶማሊያ መንደሮች የገባው የኮሌራ ተላላፊ በሽታ የዕርዳታ አቅርቦቱን ጥረት አወሳስቧል፡፡
በአምነስቲ ዘገባ መሠረት፣ በሠብዓዊ መብት አስከባሪዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ጫፍ ደርሷል።
እዚህ ናይሮቢ ውስጥ ለተኘገችው ይህቺ ሴት ይህ ቀን ትልቅ ነው፡፡ እርሷና ሌሎች ሃምሳ ሦስት በልጅነታቸው የተገረዙ ሴቶች ዛሬ ግርዛቱን የሚቀለብስ ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸዋል፡፡ “ካሊቶርኤድ”በሚል መጠሪያ ከተዋቀረው የዩናይትድ ስቴትስ ድርጅት የመጡ ዶክተሮች የሴቶቹን የተቆረጠ ብልትና በመቆረጡም ያጡትን ስሜት በቀዶ ጥገና ሊመልሱ ይሞክራሉ፡፡
አፍሪካዊ የግጭቶች አፈታት ዘዴዎች ላይ የሚወያይ ዓለምቀፍ ዓውደ ጥናት ዛሬ በመቀሌ ፕላኔት ሆቴል ውስጥ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፌዴራሉን ምርመራ ቢሮ /ኤፍቢአይ/ን ዳይሬክተር ጄምስ ኮሚን ከሥራ ኃላፊነት ለማባረር የወሰዱትን የውሳኔ እርምጃ “ትክክል ነው” ሲሉ እየሟገቱ ናቸው።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከፍተኛ ብዛት ያላቸው አፍሪካውያን ሕገወጥ በሆነ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሊብያ ጠረፍ ሲጋቡ ቆይተዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፌዴራል ምርመራ ቢሮ /ኤፍቢአይ/ ዳይሬክተሩን ጄምስ ኮሜይን ለማባረር የወሰኑት በራሣቸው ቃላት "መሥራቤቱን በተሳካ ሁኔታ ለመምራት ባለመቻላቸው" እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ 45ኛ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡ ስድሥት ወራት ሆኗል።
በፈረንሣይ ምርጫ አክራሪዋ ብሔረተኛ ማሪን ሎ ፔን በተቀናቃኛቸው ኢማኑኤል ማክሮን ድል መነሣታቸው በይፋ ከተገለፀ ገና ሁለት ቀን መሆኑ ነው፡፡
የተመራጩ የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የተስፋና የእምነት ምዕራፍ መሆን እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል፡፡ ሪፖርተራችን ሉዊስ ራሚሬዝ ከፓሪስ ያጠናቀረውን ዘገባ ሄኖክ ሰማእግዜር ያቀርበዋል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ