የብዘሃ ሕይወት ጥበቃ የተወሰኑ ቦታዎችን ለብሔራዊ ፓርክነት ወይም መናፈሻነት ከመመደብ በላይ ነው።
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ትላንት ዕሁድ ባደረጉት ንግግር የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባለት ከፓርቲያቸው አቋም ጋር ቢጣረስም ዕውነቱን መርምረው ሃቅ እንደሚናገሩ ጥልቅ ምኜቴ ነው ብለዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ትላንት ይህን አስተያየት የሰጡት ቦስተን ከተማ ውስጥ የጆን ኤፍ ኬኔዲን ፕሮፋይል ከሬጅ በቁም ትርጉሙ የፅናት ተምሳሌት የተባለ ሽልማት በተቀበሉበት ወቅት ነው፡፡
ሦስት ኢትዮጵያዊያን ሴት ልጆች በመላ ሃገሪቱ እየተዘዋወሩ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን “በአስማት” በማስቆም ላይ ናቸው። በትምህርት ቤቶችም ሴት ልጆች ዕኩል ተሳትፎ እንዲኖራቸው ምትኀታዊ ሥራቸውን ይሠራሉ። እንዴት ከማለታችሁ በፊት ነገሩ አዲስ የአሻንጉሊት ፊልም ጭብጥ ነው - አኒሜሽን። ማርተ ፋን ደርቮልፍ ከአዲስ አበባ የዘገበችውን ሔኖክ ሰማእግዜር ያቀርበዋል።
የዓለም የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ቀን አስመልክቶ የአሜሪካ ድምፁን ጨምሮ በዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ የግብር ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ የመገናኛ ብዙሃንን የሚያስተዳድረው /BBG/ ከጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ያሰናዳው ውይይት ተካሂዷል፡፡ የግልና በመንግሥት ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ የመገናኛ ብዙሃን የሚገጥሟቸውን ፈተናዎች፣ የዓለም አቀፍ የዜና ምንጮች ለማኅበረሰቦች የሚያበረክቱትን አስተዋፆዖ በተመለከተ የተሰናዳውን ውይይት ማሪያማ ዲያሎ ዘግባለች።
ሂለሪ ክሊንተን ባለፈው ኅዳር ወር በተካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከተሸነፉ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ በተደረገላቸው ቃለ መጠይቅ ለመሸነፋቸው የራሳቸውም ኃላፊነት እንዳለበት ገልፀዋል።
አልሸባብን በሁለት ዓመታት ውስጥ ለማሸነፍ የሚያስችል ስልት ማዘጋጀቱን የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ /ፋርማጆ/ አስታወቁ።
እንግሊዝ ከአውሮፓ ኅብረት ለመውጣት ከወሰነች ወዲህ አፍሪካ ውስጥ ያሉ ሃገሮችን ጨምሮ በቅኝ ይዛቸው ከነበሩ ሀገሮች ያሏትን ንግዶች ለማስፋት እያሰበች መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ የእንግሊዝን ፖሊሲ አንዳንዶች የቀድሞ ዘውዳዊ ሥርዓት ያስተዳድራቸው የነበሩ የዓለም ክፍሎችን እንደገና ለማሰባሰብ ያቀደ ዘዴ እያሉት ነው። እቅዱ ከበርካታ የአፍሪካ ሀገሮች ተቃውሞ ሊገጥመው እንደሚችል ሪፖርተራችን ሔንሪ ሪጅዌል ከለንደን ዘግቧል፡፡
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የመጀመሪያው ዙር ውጤቶች
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የኢጣልያው ጠቅላይ ሚኒስትር ፓውሎ ጄንቲሎኒ በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን ለማረጋጋት በተያዙ ጥረቶች ለመተባበርና ለዓለም ደኅንነት ዋና ስጋቶች ናቸው ያሏቸውን የኢራንና ሰሜን ኮሪያን የኑክሌር ፕሮግራሞች ለማጥፋት ስለሚቻልበት መንገድ ተወያይተዋል። የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ሀገሮችን ስምምነትና የአውሮፓ ኅብረትን ማጠናከር እንዲሁም ሽብርተኝነትን መዋጋት የሚሉት የሁለቱ መሪዎች ዓብይ አጀንዳዎች እንደነበሩም ተገልጿል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕርዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና ቀዳሚቱ ወይዘሮ ሜላኒይ ትረምፕ ዛሬ በሺኾች የሚቆጠሩ ሕፃናትና ወላጀቻቸውን ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ግቢ ውስጥ ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
ቱርክ ውስጥ ትናንት በተካሄደ ውሳኔ ሕዝብ በፕሬዚዳንት ራጂብ ጣኢብ ኤርዶዋን የሚመራው ገዥ ፓርቲ ተሳክቶለት በፈንጠዚያ ላይ ይገኛል፡፡
ከሊብያ የተነሱና ትናንት ዕሁድ በእርዳታ ደራሾች ከሜዲቴራኒያን ባህር የተረፉ ቁጥራቸው ከአንድ ሺህ በላይ የሆነ ፍልሰተኞች ከጣልያን ሲቺሊያ ደሴት ወደብ ላይ ደረሱ፡፡ ፍልሰተኞቹን ዛሬ የጣልያኗ ካታኒያ ወደብ ላይ ያደረሰችው አንዲት የጀርመን ባሕር ኃይል መርከብ መሆኗ ታውቋል፡፡
በሰሜን ናይጀሪያ የሚንቀሳቀሰው አሸባሪ ቡድን በቺቦክ ከተማ የተከሰተው ድርጊት ዓለምን ያሳዘነና ያንቀሳቀሰ ክስተት ሆኗል። አንዳንዶቹ ልጃገረዶች ረጅም ጊዜ በፈጀ ድርድር ቢመለሱም፤ ሌሎቹ እስካሁን ደብዛቸው ጠፍቷል። የናይጀሪያ ፕሬዚደንት መሃመዱ ቡሃሪ እነዚህ ሴት ልጆች ለማስመለስ እንደሚጥሩ ገልፀዋል። ልጆቻቸው የተወሰዱባቸው ቤተስቦችና በጉዳዩ ላይ የሚሰሩ ግን፤ ፕሬዚዳንቱ በዚህ ሥራ አልተሳካላቸውም ሲሉ ይተቻሉ።
በትናንትናው ዕለት ዩናይትድ ስቴትስ በጦር መሣሪያ ካዝናዋ ከኑክሌር ቦምብ ውጭ ትልቁ የተባለውን ፈንጂ በአፍጋኒስታን ጥላለች። ጥቃቱ በምሥራቃዊ አፍጋኒስታን ናንገሃር ግዛት እራሱን እስላማዊ መንግሥት ነኝ ብሎ የሚጠራው አይሲስ ይጠቀምባቸው በሚል መረጃ የተገኝባቸው ዋሻዎች ላይ ያነጣጠረ ነው። የዩናይትድ ስቴይስ ወታደራዊ ባለሥልጣናት በጥቃቱ ምን ያህል የአይሲስ ተዋጊዎችና ሠላማዊ ሰዎች እንደተገደሉ መረጃ የለንም ብለዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን በአሁኑ ወቅት ሞስኩ ይገኛሉ።
ወደ ዩጋንዳ ከሚገቡ አዳዲስ ስደተኞች ውስጥ ወዲያ ወዲህ የመዘዋወር ነፃነት ይጠበቅላቸዋል። ሀገሬውም በአብዛኛው ስደተኞችን ተቀባይ ነው። ሰሜናዊ ዩጋንዳ ከሚገኝ የስደተኞች ሰፈር የአሜሪካ ድምጿ ጂል ክሬይግ ስለዚህ ልዩ የሆነ የዩጋንዳ የስደተኛ ፖሊሲ ያጠናቀረችው ዘገባ ቆንጂት ታዮ ታቀርበዋለች
የታላቁ ኢትዮጵያዊ ጀግና የሌተናል ጀነራል ጃጋማ ኬሎ የቀብር ሥነ ስርዓት ትናንት በመንበረ ፀባዎት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል፡፡
ትናንት እሁድ ግብፅ ውስጥ በሁለት ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን ቢያንስ አርባ አራት ሰዎች ለገደሉት የቦምብ ጥቃቶች ራሱን "እስላማዊ መንግሥት" ብሎ የሚጠራው ቡድን ኃላፊነት ወሰደ፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ትናንት ሌሊት በአንድ የሶሪያ የአየር ኃይል መደብ ላይ ያደረሰችውን ጥቃት የአውሮፓ አጋሮቿ ሲደግፉ ሩሲያ የወረራ አድራጎት ነው ስትል አውግዛዋለች፡፡
በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋምና ለተረጂዎች ለመድረስ በክልሉና በፌደራል መንግሥታት እንደዚሁም ዓለምአቀፍ አጋሮች የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን የክልሉ ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሃመድ ኡማር አስታወቁ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ