የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንድን የምርጫ ውጤት ውድቅ ያደረገበትንና ተቃዋሚዎች ከምርጫ የወጡበትን ሂደት አሳልፎ እዚህ የደረሰው የዛሬው ቃለ መሓላ፣ ወደ 60,000 ሕዝብ በናይሮቢው ካሳራኒ ስታዲየም የታደመበት ነበር።
ከ44ሺህ በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ተሳታፊዎች በተካፈሉበት ውድድር፣ አትሌቶች ይገኙበት እንደነበርና፣ በውድድሩ ላይ አንደኛ ለወጡ አሸናፊዎች የመቶ ሺህ ብር ሽልማት መበርከቱ ተጠቁሟል፡፡ በዚሁ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ፣ መነሻ እና መድረሻው መስቀል አደባባይ የነበረ ሲሆን በውድድሩ ከተገኘው ገንዘብ የተወሰነ ለዕርዳታ እንደሚውልም የታላቁ ሩጫ አዘጋጆች ገልፀዋል።
የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንሲስ፣ ለሮሒንግያ ሙስሊሞች ቀውስ መፍትሔ ለማፈላለግ ዛሬ ሰኞ ማያንማር ገብተዋል፡፡
በአሜሪካዊያን ሴቶች ለዘመናት በዝምታ ያለፏቸውን የፆታ ትንኮሳዎች፣ ጉንተላዎችና አስገድዶ መደፈር ታሪኮች በይፋ እየተናገሩ፤ በተለይ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ታዋቂ ሰዎች ፈጸሟቸው የተባሉት የህዝብ መነጋገሪያ ሆኗል።
በግንቦት ሠባት ድርጅት ውስጥ በማንኛወም ሁኔታ ተሣትፋችኋል ተብለው የሽብር ክሥ የተመሠረተባቸውን ዘጠኝ ሰዎች ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ለሌላ አንድ ወር ቀጠረ፡፡
የኢትዮጵያ አይሁዶች /ቤተ እሥራኤላውያን/ በየዓመቱ የሚያከብሩት የሥግድ በዓልን በእያሩሳሌም አክብረዋል። እንደ ቤተ እሥራኤላውያን እምነት የሥግድ በዓል ከጥንታዊ የይሁድ በዓልና ወግ የተወረሰ ከብዙ ሺ ዓመታት ጀምሮ የሚያከበር ነው፡፡
የእሥያን የንግድ አቅጣጫ አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስና የቻይና ፕሬዚዳንቶች ለአካባቢው የንግድ መሪዎች ባደረጓቸው ንግግሮች ውስጥ ጨርሶ የሚጣረሱ አመለካከቶችን አንፀባርቀዋል።
በዓለም እጅግ ግዙፉ የኒው ዮርክ ከተማ ማራቶን፣ ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ ከ50 ሺሕ በላይ ተሳታፊዎች ተወዳድረዋል፡፡
ኒጀር ውስጥ በቅርቡ አራት የልዩ ኃይል አባላት ወታደሮችን ሕይወት ያጠፋው የደፈጣ ጥቃት ከሠሃራ በመለስ በሚገኘው የሳሕል ክልል ክፍሎች የፀጥታ ሁኔታው እየተዳከመ መሄዱን አመልክቷል። አምስት የሳሕል ክልል ሀገሮች ቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ፣ ሞሪታንያ፣ ኒጀርና ቻድ በአካባቢው ያለውን የአሸባሪነት አዳጋን ለመታግል የሕብረት ወታደራዊ ኃይል ለመመሥረት ስለሚያደርጉት ጥረት የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ዘጋቢ ማርያማ ዲያሎ አጠናቅራዋልች፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በ1960ዎቹ መጨረሻ ላይ በተካሄደው ቀይ ሽብር ውስጥ እጃቸው አለ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ሆላንድ ውስጥ ተይዘው አንድ የሄግ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ፣ ለብዙ ጊዜ ሲጓተት የቆየውን ምርጫ በቀጣዩ ዓመት የማታካሂድ ከሆነ፣ በድምፅ አሰጣጡ ላይ ምንም ዓይነት ዓለምቀፍ ዕርዳታ እንደማታገኝ፣ የዩናይትድ ስቴትሷ ልዑክ ኒኪ ሄሊ አስታወቁ።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለአሥራ ሁለት ቀናት የእስያ ጉብኝት ወደ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ቻይና እና ቬትናም ያመራሉ፡፡ በእስያ ፓስፊክ ሀገሮች የኢኮኖሚ ጉባዔ ላይ ይካፈላሉ፡፡ በክልሉ የሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ አጋር አገሮች ሚስተር ትራምፕን የሚያስተናግዱት በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚሆን ተጠቅሶ በመካከላቸው የሚኖረው ውይይትም በጋራ ስምምነት ላይ ያተኩርና ይልቁንም የሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ከተነሳ ጥንቃቄው ከፍ ይላል፡፡
ኬንያ ውስጥ ዛሬ የተካሄደው የፕሬዚዳንታዊ ማጣርያ ምርጫ በፖሊሶችና በተቃዋሚዎች መካከል ግጭት አስከትሏል። ተቃዋሚዎች በሚበዙባቸው አካባቢዎች ደግሞ የምርጫ ጣብያዎች ሳይከፈቱ ቀርተዋል።
በደቡብ ሱዳን የሰላም ጉዳይ ሁላችንም አንድ ድምፅ ሊኖረን ይገባል ሲሉ በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኒኪ ሄሊ ተናገሩ፡፡
ያዝነው ወር ኒጀር ውስጥ የተገደለው አሜሩካዊ ወታደር ባለቤት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለማጽናናት በስልክ ባነገሯት ወቅት የሟቹን ባለቤትዋን ስም “ላ ዴቪድ ጆንሰንን ለማስታወስ ሲንተባተቡ በመስማቴ የባሰ እንዳልቀስ አድርጎኛል” ስትል ዛሬ ተናግራለች።
የሰሜን ኮሪያ መንግሥት ላለፉት አሥርት ዓመታት ካዝናውን ለመሙላት ሲተማመን የቆየው፣ በሕገወጥ ንግድ በሚያገኘው ገንዘብ ላይ ነበር።
ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መግባት የሚከለክለው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጉዞ እገዳ፣ በሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች መሻሩ ይታወቃል።
በሶል እና በዋሽንግተን መካከል ያለው የኒውክሌር ፍጥጫ እያደር እያየለ በመጣበት ባሁኑ ወቅት፤ ለሠላማዊ መፍትሔ ያለው ተስፋ እየተመናመነ እና ወታደራዊ ግጭት የመከተሉ አደጋ በአንጻሩ መሆኑን የሰሜን ኮሪያ ጉዳይ አጥኚዎች እየተናገሩ ነው ።
ተጨማሪ ይጫኑ