ሶማሊያ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ያለው ፅንፈኛ የሁከት ቡድን አል-ሻባብ እያደረሰ ያለው አደጋ እየበዛ መምጣቱ አሜሪካ በቡድኑ ይዞታዎች ላይ የምታካሂደውን የአየር ድብደባ እንድታጠናክርና እንድታሰፋ ያስገደዳት መሆኑን ዋሺንግተን እየተናገረች ነው።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ሶማሊያ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ያለው ፅንፈኛ የሁከት ቡድን አል-ሻባብ እያደረሰ ያለው አደጋ እየበዛ መምጣቱ አሜሪካ በቡድኑ ይዞታዎች ላይ የምታካሂደውን የአየር ድብደባ እንድታጠናክርና እንድታሰፋ ያስገደዳት መሆኑን ዋሺንግተን እየተናገረች ነው።
አል-ሻባብ በሶማሊያ ወታደሮችና በጥምሩ የአፍሪካዊያን ኃይል ክፉኛ እየተመታና ብርቱ ጫና እያደረበት ቢሆንም የአፀፋ ጥቃት እጆቹን እየተሠናዘረ የከፉ ጉዳቶችን እያደረሰ ነው።
የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄነራል ዴቪድ ሮድሪጌዝ ለቪኦኤ ሲናገሩ ቁጥሩ የበዛ ሰው ሰብስበው እንደሚያሰለጥኑ፤ ከዚያም ለአሚሶም ጦር ካዋጡ ሃገሮች በአንዱ መደብ ላይ አደጋ እንደሚጥሉ አመልክተዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህ የአል-ሻባብ ዘመቻዎች የአልቃይዳው ግብር አበር ቡድን እራሱ ለአሜሪካ የአየር ድብደባዎች ቀለል ያለ ዒላማ ሆኖ እንዲጋለጥ ማገዛቸውን ጄነራል ሮድሪጌዝ ገልፀዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5