በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማልያ ውስጥ አምስት ጋዜጠኞች ባልደረቦቹ በዐል-ሸባብ እንዲገደሉ የጠቆመ ጋዜጠኛ በሞት እንዲቀጣ ተፈርዷል

ጋዜጠኞች እንዲገደሉ ለአል-ሸባብ ጠቁሟል የተባለ ጋዜጠኛ በሞት እንዲቀጣ ተፈረደበት
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:23 0:00

ጋዜጠኞች እንዲገደሉ ለአል-ሸባብ ጠቁሟል የተባለ ጋዜጠኛ በሞት እንዲቀጣ ተፈረደበት

የፍርድ ቤቱ ብይን እንደሚለው ሐሰን ሀናፊ እአአ ከ 2007 እስከ 2011 ዓ.ም. በነበረው ጊዜ ውስጥ ኢላማ ሊሆኑ የሚችሉ ጋዜጠኞችን በመጠቆም ተግባር ጽንፈኛውን ቡድን ሲረዳ ቆይቷል።

በሶማልያ መዲና ሞቃዲሹ ያለ ወታደራዊ ችሎት አምስት ባልደረቦቹ የሆኑ ጋዜጠኞች በዐል-ሸባብ እንዲገደሉ የጠቆመ ጋዜጠኛ በሞት እንዲቀጣ ተፈርዷል።

የፍርድ ቤቱ ብይን እንደሚለው ሐሰን ሀናፊ እአአ ከ 2007 እስከ 2011 ዓ.ም. በነበረው ጊዜ ውስጥ ኢላማ ሊሆኑ የሚችሉ ጋዜጠኞችን በመጠቆም ተግባር ጽንፈኛውን ቡድን ሲረዳ ቆይቷል።

መሐመድ ሹት የተባሉ የወታደራዊው ችሎት ሊቀመንበር በተከሳሹ ላይ የቀረቡ ማስረጃዎች ሁሉ በአምስቱ ጋዜጠኞች ግድያ ውስጥ እጁ እንዳለበት አመልክተዋል ብለዋል።

“የዐል ሸባብ አባል እንደሆነ ካረጋገጥን በኋላ ለግድይ ኢላማ ሊሆኑ የሚችሉ ጋዜጠኞችን በመጠቆም ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ተገኘ” ብለዋል ሹት።

ሐሰን ሀናፊ አይኪውኬ (IQK) በተባለ ከስምንት አመታት በፊት አል-ሸባብ በያዘው ሬድዮ ጣብያ ይሰራ ነበር። አቻ አምና ነሃሴ ወር ላይ የኬንያ የጸጥታ ሃይሎች አስረው ለሶማልያ መንግስት አስረከቡት።

ሶማልያ ላይ በስምንት አመታት ውስጥ 25 ጋዜጠኞች እንደተገደሉ ለጋዜጣኞች መብት የሚሟገተው ሲፒጄ (CPJ) ገልጿል።

XS
SM
MD
LG