በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማልያ ያለው የአፍሪቃ ህብረት የሰላም ጥበቃ ተልእኮ በዐል ሸባብ ላይ ድል እያገኘ እንደሆነ ገለጸ


ሶማልያ ውስጥ የአፍሪቃ ህብረት ሰላም ጥበቃ ተልእኮ እንቅስቃሴዎች ሀላፊ ከቅርብ ወራት ወዲህ ወታደሮቹ ተግዳሮቶች ቢገጥሟቸውም የሰላም ጥበቃው ተልእኮ የበላይነቱን እንደጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል። ዓል ሸባባ ባካሄዳቸው ጥቅቶች በርካታ ሰለም ጠባቂ ወታደሮች እንደተገደሉ የሚታወቅ ነው።

ሶማልያ ውስጥ የአፍሪቃ ህብረት ሰላም ጥበቃ ተልእኮ (AMISOM) እንቅስቃሴዎች ሀላፊ Francisco Caetano Madeira የተልእኮው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ዐል ሸባብን ለማሸነፍ አልቻለም የሚለውን አባባል አስተባብለዋል።

“አሚሶም በሚገባ እያሸነፈና ዐል-ሸባብን እያሯሯጠ ነው። ዐል-ሸባብ ህልውናውን ለመጠበቅ ሲል ራሱን በአዲስ መልክ ለማዋቀር ተገዷል። የሶማልያ መንብስት የደቡብ ማዕከላዊ ሶማልያ 80 ከመቶ ክፍልን ይቆጣጣራል። ይህም አል-ሸባብ ከነዚህ ይቆጣጠራቸው ከነበሩት ቦታዎች መባረሩንና እኛ በሚገባ እያሸንፍን መሆናችንን ያሳያል።”

አል-ሸባብ ቢያንስ በሶስት የአፍሪቃ ህብረት ተልእኮ ሰፈሮች ላይ ባካሄአደው ጥቃት ምክንያት የአሚሶም ወታደሮች ከተወሰኑ ከተማዎች መውጣታቸው አንዳንድ የሶማላያ ባለስልጣኖችንና የአከባቢው ጠበበትን አሳስቧል። ለምሳሌ ጽንፈኛው ቡድን ባለፈው ወር ኤል-አደኤ በተባለቸው ከተማ ላይ በከፈትው ጥቃት ከ 100 በላይ የሚሆኑ ኬንያውያን ወታደሮች ተገድለዋል።

Madeira ግን አሚሶም ከከተማዎች እየወጣ ነው የሚለውን ወሬ አጥብቀው አስተባብለዋ።”ወታደሮችንን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ የማንቀሳቀሱ ተግባር ለታክቲክ የሚደረግ የወታደራዊ ስትራቴጂ አካል ነው ብለዋል።

የአሚሶም ወታደሮች ማርካ ከተባለችው ስትራቴጃዊ የወደብ ከተማ ለአጭር ጊዜ ከወጡ በኋላ የዐል-ሸባ አማጽያን ገብተው ከአሚሶምና ከሀገሪቱ መንግስት ጋር ይሰራሉ በሚል የተረጠርዋችውን ሰዎች ገድለዋል። አንዳንድ የሶማልያ ባለስልጣኖች ታድያ ተልእኮው በህዝቡ ላይ ያለውን እምነት ሸርሽሯል ሲሉ ነቅፈው ነበር።

ባለፈው ወር ኤል-አዴ በተባልችው ከተማ ላይ ከተከፈተው ጥቃት ጋር በተያያዘ ከአከባቢው ህዝብ ጋር ያለውን ግንኙነት በሚመለከት የኬንያ ባለስልታኖች ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ማደይራ ግን ኤል-አዴ ላይ የተፈጸመው ጥቃት የዐ-አልሸባ ተግባር እንጂ የህዝቡ አይደለም። ስለሆነም ከህዝቡ ጋር ችግር የለብንም። ከአከባቢው ባለስልጣኖች ጋር በበለጠ ተቀራርበን ነው መስራት ያለብን ብለዋል።

አሚሶም መቼ ነው ከሶማልያ የሚወጣው ለሚለው ጥያቄም ማደይራ ሶማሊዎች እንዲወጣ ሲጠይቁትና ተልእኮውን ሲያጠናቅቅ ነው ሲሉ መልሰዋል።

በአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የሶማልያ ክፍል ዘጋቢ ሀሩን ማሩፍ Francisco Caetano Madeira ን አነጋግሯል። አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።

ሶማልያ ያለው የአፍሪቃ ህብረት የሰላም ጥበቃ ተልእኮ በዐል ሸባብ ላይ ድል እያገኘ እንደሆነ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:47 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG