በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ጊቢ የውሃና መብራት መቋረጥ ተቃውሞ አስነሳ

አምቦ ዩኒቨርስቲ

በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ግቢ ካለፈው አርብ ጀምሮ ውሃ መቋረጡን፣ መብራት ከዕረቡ ጀምሮ መጥፋቱን እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ከሠላሳ በላይ ሰዎች መታሠራቸው በዚህ ዘገባ ተካቷል።

በዕረቡ ምሽት ዘገባችን ካለፈው አርብ ጀምሮ ውሃ በመቋረጡ ምክንያት ችግር ውስጥ መኾናቸውን የገለጹት አምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ግቢ ተማሪዎች በተጨማሪም መብራት እንደተቋረጠና ይህንንም ተከትሎ የግቢው ተማሪዎች በሙሉ ተቃውሞ ሲያቀርቡ አስለቃሽ ጭስ እንደተወረወረባቸውና እንደተደበደቡ አንዳንድ ተማሪዎች ገለጹ፡፡

የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ባልደረባ ጃለኔ ገመዳ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች።

Your browser doesn’t support HTML5

በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ጊቢ የውሃና መብራት መቋረጥ ተቃውሞ አስነሳ

አምቦ ዩኒቨርስቲ /ከዩኒቨርስቲው ዌብሳይት የተገኘ ፎቶ/

የውሃ መቋረጥ በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ግቢ

በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ግቢ ካለፈው አርብ ጀምሮ ውሃ በመቋረጡ ተማሪዎች የሚጠጡትም ኾነ የሚታጠቡበት እንደሌላቸው፣ በመፀዳጃ ቤቶቹም ውሃ ስለሌ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መኾናችውን ተማሪዎች ገለጹ፡፡

ይህ ችግር እንዲቃለል ተቃውሞ ቢያቀርቡም በአስለቃሽ ጭስ እንደተበተኑ ይናገራሉ፡፡

የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ባልደረባ ጃለኔ ገመዳ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች።

Your browser doesn’t support HTML5

የውሃ መቋረጥ በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ግቢ

አምቦ ዩኒቨርስቲ /ከዩኒቨርስቲው ዌብሳይት የተገኘ ፎቶ/

በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ከሠላሳ በላይ ሰዎች መታሠራቸውን ተማሪዎች ተናገሩ

በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ውስጥ ሰኞ እና ማክሰኞ በተማሪዎችና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ግጭት መፈጠሩን ነዋሪዎች ገለጹ። ከግጭቱም በኋላ ከሰላሳ ሰው በላይ መታሰሩን ተናግረዋል። የከተማው ፖሊስ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ይላል።

የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ባልደረባ ቱጁቤ ኩሳ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች።

Your browser doesn’t support HTML5

በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ከሠላሳ በላይ ሰዎች መታሠራቸውን ተማሪዎች ተናገሩ