ዋሽንግተን ዲሲ —
ይህ የከተሞች ዐዋጅ በክልሉ ከተጀመረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ መነሻዎች አንዱ መኾኑ ይታወቃል። አንቀጾቹ የተሠረዙት ጉዳት ስላላቸው ሳይሆን በሕዝቡ ጥያቄ ስለተነሳባቸው መሆኑን የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል የዐዋጁ ሦስት አንቀጾች መሰረዙ የሚያመጣው አዲስ ነገር እንደማይኖር፣ ሕዝቡ ስላልተቀበለው ሙሉ በሙሉ መሰረዝ አለበት፤ "ጠቃሚ ኾኖ ቢገኝ እንዃን ሕዝብ ስላልተወያየበት ተቀባይነተ ሊኖረው አይገባም።" ሲሉ የኦሮሞ ፌዴራሊስ ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ማምሻውን ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል።
ጽዮን ግርማ አነጋግራቸዋለች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።