በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ በአፍሪካ

በዐማራ ክልል በዋግ ኽምራ ዞን በሰሀላ ሰየምት ወረዳ፣ በ2015/16 የመኸር ምርት ዘመን የተከሠተው የዝናም እጥረት ባስከተለው ከባድ ድርቅ፣ ከአራት ሺሕ በላይ የቤት እንስሳት እንደሞቱና በሚሊዮን የሚቆጠሩትም ወደ አጎራባች አካባቢዎች እየተሰደዱ እንደኾኑ ተገለጸ፡፡

የዞኑ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ምሕረት መላኩ፣ ዛሬ ረቡዕ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ከ22 ግብረ ሠናይ ድርጅቶች እና ከመንግሥታዊ ተቋማት ተወጣጥቶ የተቋቋመው የጥናት ቡድን ወደ ወረዳው አምርቶ፣ ድርቁ ያስከተለው ችግር ከፍተኛ እንደኾነ አረጋግጧል፡፡

ያነጋገርናቸው የሰሀላ ሰየምት ወረዳ ምሽሀ ቀበሌ አርሶ አደሮችም፣ የቤት እንስሶቻቸው በመሞታቸው ለፈታኝ ሕይወት እንደተዳረጉ አመልክተዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

በሰሀላ ሰየምት ወረዳ በጸናው ረኀብ የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:47 0:00

በዐማራ ክልል በዋግ ኽምራ ዞን በመኸር ዘመኑ የተከሠተውን ድርቅ ተከትሎ፣ በሰሀላ ሰየምት ወረዳ ከጸናው ረኀብ ጋራ በተያያዘ የሚሞተው ሰው ቁጥር እንደጨመረ፣ አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን ተናገሩ፡፡

በወረዳው የብላዛ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ማለደ ብሬ፣ ባለፈው ወር ከረኀብ የተነሳ የአራት የቀበሌው ነዋሪዎች ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል፡፡ ከዚያም ወዲህ የርዳታ እህል ባለመቅረቡ፣ ባለፈው ሳምንት ሁለት ተጨማሪ ሕፃናት እንደሞቱ ገልጸዋል፡፡

ስለ ጉዳዩ የተጠየቀው፣ የዐማራ ክልል የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን፣ በዞኑ የረኀብ አደጋ ወደ አንዣበባባቸው አካባቢዎች የዕለት ርዳታ ተልኳል፤ ብለዋል፡፡

የዋግኽምራ ዞን የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በበኩሉ፣ የርዳታ እህል መላኩን ጠቅሶ ነገር ግን ከተረጂው ቁጥር አንጻር አነስተኛ እንደኾነ አመልክቷል፡፡ ከገባሬ ሠናይ ድርጅቶች ተጨማሪ ርዳታ ለማሰባሰብም፣ የጸጥታው ችግር ዕንቅፋት እንደኾነበት አክሏል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG