በዐማራ ክልል በዋግ ኽምራ ዞን በመኸር ዘመኑ የተከሠተውን ድርቅ ተከትሎ፣ በሰሀላ ሰየምት ወረዳ ከጸናው ረኀብ ጋራ በተያያዘ የሚሞተው ሰው ቁጥር እንደጨመረ፣ አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን ተናገሩ፡፡
በወረዳው የብላዛ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ማለደ ብሬ፣ ባለፈው ወር ከረኀብ የተነሳ የአራት የቀበሌው ነዋሪዎች ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል፡፡ ከዚያም ወዲህ የርዳታ እህል ባለመቅረቡ፣ ባለፈው ሳምንት ሁለት ተጨማሪ ሕፃናት እንደሞቱ ገልጸዋል፡፡
ስለ ጉዳዩ የተጠየቀው፣ የዐማራ ክልል የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን፣ በዞኑ የረኀብ አደጋ ወደ አንዣበባባቸው አካባቢዎች የዕለት ርዳታ ተልኳል፤ ብለዋል፡፡
የዋግኽምራ ዞን የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በበኩሉ፣ የርዳታ እህል መላኩን ጠቅሶ ነገር ግን ከተረጂው ቁጥር አንጻር አነስተኛ እንደኾነ አመልክቷል፡፡ ከገባሬ ሠናይ ድርጅቶች ተጨማሪ ርዳታ ለማሰባሰብም፣ የጸጥታው ችግር ዕንቅፋት እንደኾነበት አክሏል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም