በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በልጅነት የሚደርስ የመስማት ችግርን መከላከል እንደሚቻል ተገለፀ


ፋይል ፎቶ - የሦሥት አመቷ የኢራቅ ተወላጇ ህጻን አሚና መስማት ለማስቻል የሚሞከርበትን ፈተና እየተፈተነች እያለ ስትስቅ የተነሳ ፎቶ
ፋይል ፎቶ - የሦሥት አመቷ የኢራቅ ተወላጇ ህጻን አሚና መስማት ለማስቻል የሚሞከርበትን ፈተና እየተፈተነች እያለ ስትስቅ የተነሳ ፎቶ

የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት WHO 60 በመቶ የሚሆነው መስማት የተሳናቸው ሕፃናትን ችግር ለመከላከል የሚያስችል አዲስ ጥናት እንደተገኘ አስታውቋል። በዛሬው እለት በሚከበረው አመታዊ “የመስማት ቀን” ህፃናት የሚያጋጥማቸውን የጆሮና የመስማት ችግር እንዴት መከላከል እንደሚቻል WHO ሲወያዩበት ቆይተዋል።

አለም አቀፉ የጤና ድርጅት WHO እንደዘገበው በአለማችን 360 ሚልየን የሚሆነው ህዝብ የመስማት ችግር ይገጥመዋል ከዚህ ቁጥር ውስጥ ደግሞ 32 ሚልየን የሚሆኑት ህፃናት ናቸው። ከ 32 ሚልየኑ ውስጥ ደግሞ 31 ሚልየኑ በመካከለኛና በዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ያሉ ናቸው።

አላርኮስ ኬይዛ (Alarcos Cieza) በአለም አቀፉ የጤና ድርጅት WHO የመስማትና የማየት ችግሮችን ለመከላከል የሚደረገው እንቅስቃሴን በመምራት ላይ ይገኛሉ። 40 በመቶ የሚሆኑት በልጅነታቸው የመስማት ችግር የሚገጥማቸው ከቤተሰብ በሚተላለፍ በሽታ ሲሆን 31 በመቶየሚሆኑት ደግሞ በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት ነው።

"ልጆች በተለያዩ በሽታዎች በቀላሉ መጠቃታቸው የታወቀ ነው፤ ለምሳሌ እንደ ጆሮ ደግፍ፣ ማጅራት ገትር እና ኩፍኝ ወይም ሁልጊዜ ልጆች ላይ የሚከሰተው የጆሮ ማመርቀዝ የተለመዱ በሽታዎች ናቸው። ለዚህ መፍትሄ የሚሆነው ደግሞ አስቀድሞ ለልጆቹ ክትባት መስጠት ከዛም ካለፈ ለልጆቹ በቂ ህክምና እንዲያገኙ በማመቻቻት ነው።" አንድ አምስተኛ የሚሆኑት ሕፃናት የመስማት ችግር የሚገጥማቸው በወሊድ ጊዜ ነው። ይህን ደግሞ መከላከል ይቻላል። የመስማት ችግር ያለባቸውን ልጆች በቅርበት ከወላጆች ጋር የተሻለ መረጃን በመለዋወጥና የህክምና እርዳታ የመስጠት እንቅስቃሴ በቅርቡ እንደሚጀመር አላርኮስ ኬይዛ ተናግረዋል።

አላርኮስ ኬይዛ ጨምረው እንደተናገሩት መቶ በሚሆኑ በመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሃገሮች እየተከሰተ ያለውን የመስማት ችግር ለመቅረፍ ሰፊ እቅድ ተይዟል። በተለይም የመስማት ችግሩ ከመባባሱ በፊት ለልጆቹ ህክምና ማድረግና የመስማት ችሎታቸውን ከቀነሰ በኃላም መስማት የሚያስችላቸውን የመርጃ መሳሪያ ለማዳረስ ነው የታሰበው።

ይህን ማድረግ ካልተቻለም የምልክት ቋንቋን በማስተማር ህይወታቸውን በቀላሉ የሚመሩበትን መንገድ ለማመቻቸት ታቅዷል። ዝርዝሩን ከበታች ያለውን ድምፅ በመጫን ያድምጡ።

በልጅነት የሚደርስ የመስማት ችግርን መከላከል እንደሚቻል ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:59 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG