በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶሪያ ጉዳይ የቪየናው ምክክር አልያዘም


የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይሚንስትር ጆን ኬሪ
የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይሚንስትር ጆን ኬሪ

“በሶሪያ በሚታየው ሁኔታ አንዳችንም አረጋጊ ስሜት ጨርሶ ሊያድርብን አይችልም። እጅግ አዋኪ ነው። የተኩስአቁሙን ፈተና ላይ የጣለውና እየከፋ በመጣው የሰሞኑ ቀውስ ሁላችንንም በእጅጉ አሳስቦናል። ይሄን ሁሉ በወረቀት ላይ ከሰፈሩ ቃላት በላይ እውን ለማድረግ፤ ዛሬ ያረቀቅናቸውን በየደረጃው የሚከናወኑ ዕቅዶች ዳርማድረስ የሚያስችሉ ግልጽና በቁርጠኝነት የተመሉ ተጨባጭ እርምጃዎችን ይጠይቃል።” የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይሚንስትር ጆን ኬሪ።

በዩናይትድ ስቴትስ እና በሩሲያ የተመራውና 17 አገሮች ያሉበት ዓለም አቀፉ የሶሪያ ድጋፍ ሰጪ ቡድን ለተቋረጠው የጄኔቫው የተፋላሚ ወገኖች ንግግር ማንሰራራት መንገድ ይጠርጋል የሚል ተሥፋ ቢያሳድርም ስምምነት ላይ ሳይደርስ ቀርቷል።

ይሁንና ደራሽ እርዳታ በውጊያው ወደተጠመዱት አካባቢዎች ለማድረስ የሚያስችል መንገድ በአፋጣኝ ለመክፈትና ግጭቶቹሙሉ በሙሉ እንዲቆም የሚጠይቅ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ የቪየናው ጉባኤ ሲጠናቀቅ ባሰሙት ንግግር ሁለት ወራት በሞላው የተኩስ አቁም ላይ አደጋ ስላጠላውና እየጨመረ ስለመጣው ቀውስ ተናግረዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ እና በሩሲያ የተመራ 17 አገሮች ያሉበት ዓለም አቀፉ ጉባኤ
በዩናይትድ ስቴትስ እና በሩሲያ የተመራ 17 አገሮች ያሉበት ዓለም አቀፉ ጉባኤ

አምስት ዓመት ያስቆጠረውን የሶሪያው ቀውስ ተፋላሚ ወገኖች ያስጠነቀቁት የጉባኤው ተሳታፊዎች፤ የተኩስ አቁሙን ደጋግሞ መጣስ ስምምነቱ የሚሰጠውን ጥበቃ ጨርሶ እንዳያሳጣ ያላቸውን ሥጋት ገልጠዋል።

የተባበሩት መንግስታት የሶሪያ ልዩ መልዕክተኛ ስተፋን ደ ሚስቱራ በበኩላቸው ሲያስረዱ ደራሽ እርዳታ ወደ ሁሉምበውጊያው ወደተጠመዱ አካባቢዎች ለማድረስ ለግንቦት 24 ቀነ ገደብ ተይዟል፤ ብለዋል።

የአሜሪካ ድምጹ ቪክተር ቢቲ (Victor Beattie) ያጠናቀረውን ዘገባ፣ አሉላ ከበደ አቅርቦታል ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

በሶሪያ ጉዳይ የቪየናው ምክክር አልያዘም
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:07 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG