በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶሪያ የሰላም ድርድር እንደገና ተጀመረ


የሶሪያ የሰላም ድርድር ዛሬ ጄኔቫ ላይ እንደገና ተጀምሯል፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት የመፍጠር ጥረት ክፋት አሣቢዎች ሊያደናቅፉት ውስጥ ውስጡን ጥረት ሊያደርጉ እንደሚችሉ ስቴፋን ዴ ሚስቱራ አስታውቀዋል፡፡

የሶሪያ የሰላም ድርድር ዛሬ ጄኔቫ ላይ እንደገና ተጀምሯል፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት የመፍጠር ጥረት ክፋት አሣቢዎች ሊያደናቅፉት ውስጥ ውስጡን ጥረት ሊያደርጉ እንደሚችሉ ስቴፋን ዴ ሚስቱራ አስታውቀዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሶሪያ ጉዳይ ልዩ ልዑኩ ዴ ሚስቱራ እንዲህ ዓይነቶቹ ጥረቶች እንዲያውም ይበልጥ እንደሚያጠነክሯቸውና ለአውዳሚው ጦርነት የፖለቲካ መፍትኄ ለማስገኘት በፅናት እንዲሠሩ እንደሚያደርጓቸው ገልፀዋል፡፡

የሦሪያ ተፋላሚ ወገኖች ፊት ለፊት ተገናኝተው ለመነጋገር አሻፈረን እያሉ ነው፡፡ በመሆኑም ሁለቱንም ለማቀራረብ እየጣሩ ያሉት የመንግሥታቱ ድርጅት መልዕክተኛ ስቲቨን ዴ ሚስቱራ የአንዱን ሃሣብ ወደሌላው፤ የዚያኛውን ወደዚያኛው እየወሰዱ የማሸማገሉንና የመመካከሩን ሥራ እያከናወኑ ነው፡፡ ሁኔታው ትርጉም ያላቸውን ጭብጦች እያነሱ ለመምከር እክል እንደማይገጥማቸው ልዑኩ ተናግረዋል፡፡

ንግግሮቹ ሦሪያን ማስተዳደር፣ አዲስ ሕገመንግሥት መቅረፅ፣ በመጭው አንድ ዓመት ከመንፈቅ ውስጥም የችግሮቹ ሁሉ መፍቻ እናት ብለው የጠሩትን የሽግግር መንግሥት መምረጥ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ነው የሚያተኩሩት፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት በተካሄደው ጦርነት 250 ሺህ ሰው ተገድሏል፡፡ ግማሽ ያህሉ ሕፃናት የሆኑበት ከ6.5 ሚሊየን በላይ ቁጥር ያለው ሰው በሃገር ውስጥ ተፈናቅሏል፡፡ ከሦስት ሚሊየን በላይ ሦስት ሰው ሃገር ጥሎ ተሰድዷል፡፡

“ለተጀመሩት ድርድሮች መሳካት ሌላ አማራጭ የለውም፤ ሌላው አማራጭ እንዲያውም ወደ ከፋ ጦርነት መዘፈቅ ነው” ብለዋል ዴ ሚስቱራ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የሶሪያ የሰላም ድርድር እንደገና ተጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:00 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG