በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶሪያ መንግስት በጦርነት ለተጎዱት እርዳታ እንዳይገባ እንቅፋት መሆኑ ተነገረ

ፋይል ፎቶ - የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ አማካሪ ጃን ኤግላንድ (Jan Egeland) የስደተኞችን ካምፕ በሚጎበኙበት ወቅት ሶርያዊ ህጻን ይዘው፣ በማረጅ ከተማ ባካ ቫሊ በተባለ ቦታ ምስራቅ ሌባኖስ እ.አ.አ. 2015
ፋይል ፎቶ - የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ አማካሪ ጃን ኤግላንድ (Jan Egeland) የስደተኞችን ካምፕ በሚጎበኙበት ወቅት ሶርያዊ ህጻን ይዘው፣ በማረጅ ከተማ ባካ ቫሊ በተባለ ቦታ ምስራቅ ሌባኖስ እ.አ.አ. 2015

የሶሪያ መንግስት በጦርነት ለተጎዱት የሰብአዊ እርዳታ እንዳይታደል ፈቃድ ከለከለ ሲሉ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለስልጣን አማረሩ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ አማካሪ ጃን ኤግላንድ (Jan Egeland) እንደገለጹት በጦርነት ቀጠና ዉስጥ ለሚገኙና ሊደረሰባቸዉ ከባድ የሆነ 287,000 ለሚሆኑ ሶሪያዉያን የእርዳታ ቁሳቁስ ለማድረስ ላለፉት አራት ቀናት ካገሪቱ መንግስት ፈቃድ ማግኘት አልተቻለም።

የሶሪያ ተቃዋሚዎችም የእርዳታ እህል እንዳያልፍ መንገድ እንደሚዘጉ ባለስልጣኑ የገለጹ ሲሆን ጦርነት ከሚካሄድባቸዉ አስራ ስምንት አካባቢዎች አስራ አምስቱ መንግስት ቁጥጥር ሥር ስለሚገኙ ዋናዉ ተጠያቂ መንግስት ነዉ ብለዋል።

ሰፋ ያለ ዝርዝር ባልደረባችን ሊሳ ሽላይን አጠናቅራ የዘገበችውን ትዝታ በላቸው አቅርባዋለች፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

የሶሪያ መንግስት በጦርነት ለተጎዱት እርዳታ እንዳይገባ እንቅፋት መሆኑ ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:12 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG