በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሦሪያን የሰላም ስምምነት በሚጥስ ወገን ላይ ብቸኛ እርምጃ እንደምትወስድ ሩሲያ ዛሬ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች

ሩሲያ ይህን እርምጃ እንደምትወስድ ያስታወቀችው፥ በሦሪያ የሚካሄዱ ጥሰቶችን በጋራ ለመቆጣጠር በሚያስችሉ መመሪያዎች ላይ አብሮ ለመሥራት፥ ዩናይትድ ስቴትስ ዘግይታለች የሚል ስሞታ ከሞስኩ በሚሰማበት ወቅት ነው።

በሦሪያ አንድ ወር ሊሞላው የተቃረበውን የሰላም ስምምነት በሚጥስ ወገን ላይ በግል ብቸኛ እርምጃ እንደምትወስድ ሩሲያ ዛሬ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።

ሩሲያ ይህን እርምጃ እንደምትወስድ ያስታወቀችው፥ በሦሪያ የሚካሄዱ ጥሰቶችን በጋራ ለመቆጣጠር በሚያስችሉ መመሪያዎች ላይ አብሮ ለመሥራት፥ ዩናይትድ ስቴትስ ዘግይታለች የሚል ስሞታ ከሞስኩ በሚሰማበት ወቅት ነው።

ሩሲያና ዩናይትድ ስቴትስ፥ የሦሪያ መንግሥት ደጋፊዎችና ሽምቅ ተዋጊዎች መካከል የሚካሄደውን ውጊያ ለማስቆም ቁልፍ ሚና መጫወታቸው ይታወቃል።

በሦሪያ የዓለሙ ድርጅት ልዩ ልዑክ ስቴፋን ደ ሚስቱራ (Staffan de Mistura) ትላንት ሲናገሩ ማንኛውም ዓይነት በሩሲያና ዩናይትድ ስቴትስ ትብብር ላይ የሚደርስ እንቅፋት በጥልቅ ያሳስበኛል ብለዋል።

የሦርያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ዋሊድ ሙለም ( Walid Muallem) ንግግር እያደረጉ
የሦርያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ዋሊድ ሙለም ( Walid Muallem) ንግግር እያደረጉ

XS
SM
MD
LG