ዋሽንግተን ዲሲ —
በሦሪያ ሰላም ጉዳይ ከነገ፤ ረቡዕ ጀምሮ አዲስ የውይይት ዙር ጄኔቫ ላይ ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ባለበት ሁኔታ ሃገሪቱ ውስጥ ያለው ሁከት እየበረታ መጥቷል።
የመንግሥቱ ኃይሎችና አጋሮቻቸው አሌፖ ላይ ከተቃዋሚዎቹ ጋር እየተታኮሱ ሲሆን ሆምስ ክፍለሃገር ውስጥ ደግሞ በአማፂያኑ በተያዙት አካባቢዎች የሦሪያ የአየር ድብደባ ቀጥሏል።
በሩሲያ አየር ኃይል የደጀን ድጋፍ እያገኙ ያሉት የሦሪያ ወታደሮች በአማፂያኑ የተያዘችውን አሌፖን ከብበዋል።
የዛሬ አንድ ወር ተኩል አካባቢ፤ የካቲት 19 ተደርሶበት የነበረው ተኩስ የማቆም ውል ፈርሷል፡፡ ሁለቱም ወገኖች በብርቱ ተኩስ እየተተጋተጉ ነው፡፡ ለፊርማው መረገጥ ሁለቱም የሚወነጅሉት ሌላኛውን ወገን ነው።
ዩናይትድ ስቴትስ ለሁለቱም ወገኖች ያላት ግብዣ “እባካችሁ፤ ትንቅንቃችሁን አቁማችሁ ሁለታችሁም የበለጠ ሥጋት በሆነው ሽብር ፈጠራንና የሽብር ቡድኖችን በመዋጋት ላይ አተኩሩ” የሚል ነው።
ዛልቲካ ሆኬ የላከችውን ዝርዝር ሰሎሞን አባተ አቅርቦታል፣ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።