በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴይስ ከኢትዮጵያ ጋር በምታደርገው ንግድ የዲያስፖራው ተሳትፎ ሶስት እጅ ይሆናል


በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴይትስ ኢምባሲ
በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴይትስ ኢምባሲ

የዩናይትድ ስቴይትስ የንግድ መስሪያ ቤት ወኪል በአዲስ አበባ ከሚገኘው የዩናይትድ ስቴይትስ ኢምባሲ ከጋቢና ቪኦኤ ባደረጉት ቃለ ምልልስ በሁለቱም ሀገሮች የንግድ ድርጅቶቻቸውን ለውጭ ገበያ ዝግጁ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ዩናይትድ ስቴይትስ በአፍሪካ ሀገሮች ትልቁን መዋእለንዋይ አፍሳሽና አልሚ ሀገር ናት። የሚበዙት በእርዳታና በመሰረታዊ የትምህርትና ጤና ዘርፍ የሚውል ነው።

የንግድ ግንኙነት ግን አሁንም ቢሆን በርካታ ስራ የሚጠበቅበት ነው። ይህንን በመረዳት የዩናይትድ ስቴይትሱ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች የንግድ ቢሮዎች በማቋቋም ላይ ናቸው።

የዩናይትድ ስቴይትስ የንግድ ተቋማት በአፍሪካ ያላቸውን የንግድ ተሳትፎ ለማሳደግ ፕሬዝደንት ኦባማ አራት የንግድ ቢሮዎች እንዲከፈቱ ባዘዙት መሰረት የአዲስ አበባው ቀዳሚ ሆኖ ተከፍቷል። ሌሎቹ በታንዛንያ፣ በሞዛምቢክና አንጎላ የተከፈቱ ናቸው።

ከዩናይትድ ስቴይትስ የንግድ ምንስቴር አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ታንያ ኮል አሜሪካ ከኢትዮጵያና ከአፍሪካ ጋር ለመናገድ የያዘቻቸውን ጥረቶች ያብራራሉ።

“በንግድና ኢንቨስትመንት መሰማራት የሚፈልጉ የአሜሪካ ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ ባለሃብቶች ጋር እንዲሰሩ እናገናኛቸዋለን። ሁሉም ሰው የሚረዳውና፣ ደግሞ ተደጋግሞ የሚነገር አንድ ሃቅ፤ በአፍሪካ የንግድ ስራ ለመጀመር፤ ወደዚህ መምጣት ያስፈልጋል። ወኪል ወይንም የኢሜይል አድራሻ አይደለም በአካል እዚህ መገኘትና አጋር መፈለግ ያሻል።” ብለዋል።

የአፍሪካ ገበያ ውስጥ የዩናይትድ ስቴይትስ ኩባንያዎች እንዲሳተፉ በኮንግረስና በኦባማ አስተዳድር ከፍተኛ ፍላጎት አለ። ይህንን ፍላጎት ለማሳካት የተያዙ የህግና አሰራር ማሻሻያዎች አሉ። ዩናይትድ ስቴይትስ ለአፍሪካ የሰጠችው ከማንኛውም ዓይነት ታሪፍ ነጻ የሆነ የገበያ AGOA እንዲሁም በዩናይትድ ስቴይትስ ኮንግረስ የረቀቀው ከአፍሪካ ጋር ያለውን ንግድ በሁለት እጥፍ ለማሳደግ ያለም ህግ መጥቀስ ይቻላል።

ታንያ ኮል የአፍሪካ ሀገሮች ከነችግሮችና ፈተናዎቻቸው ለስራ በራቸውን መክፈታቸው እድል ፈጥሯል ይላሉ። “በአፍሪካ በርካታ የንግድ ስራ እድሎች አሉ። ኢትዮጵያ በዓለም በፍጥነት በማደግ ያለች ሀገር ናት፤ በአፍሪካም እንዲሁ። ስለዚህ ብዙ የስራ መስኮች አሉ።”

ሆኖም ፈተናዎቹ ገና ከጅምሩ በርካታ መሆናቸውን ነው፤ ባለሙያዎችና የንግድ ስጋት ግምገማ አቅራቢዎች የሚያስረዱት። ከቼክኖሎጂ አንስቶ (ማለትም የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት ደካማነት) የአሰራር ብቃትና ቅልጥፍና፤ በዙ ስራዎች የሚያስፈልጋቸው ናቸው። የዩናይትድ ስቴይሷ የንግድ ቢሮ ባለሙያ ታንያ ኮል ለኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ የሚተላለፈውን መልእክት ሲገልጹ፤ “የአገልግሎት ዘርፉ ከመንግስት ቁጥጥር ነጻ ሆኖ የግል ዘርፍ ተሳትፎ ይኑርበት” ብለዋል።

ከዩናይትድ ስቴይትስ ከሚመጡት ኩባንያዎች ወሳኝ ከሆኑ መካከል በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን ናቸው። ከሶስት እጅ በላይ ይሆናሉ።

ወደ 250 አሜሪካዊያን ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እኛ ድረስ መጥተዋል። ከነዚህ መሃል 35 ከመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊ ትውልድ ያላቸው አሜሪካዊያን የንግድ ድርጅቶች ናቸው። ብዙዎቹ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ተቋማት ናቸው።
አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ የዩናይትድ ስቴይትስ የንግድ ምንስቴር ታንያ ኮል

እነዚህ ኩባንያዎች ማለት ኢትዮ-አሜሪካዊያኑ የሀገሩን ባህልና አሰራር ስለሚያውቁ ወደ ኢምባሲው በመሄድ አንዳንድ ጥቅል መረጃዎችን፤ ማለትም የአዋጭነትና ህጋዊ ጥናቶችና የመሳሰሉትን መረጃዎች ሊያገኙ ይችላሉ።

በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴይትስ መካከል የሁለትዮች ንግድ እንዲስፋፋ፤ ግንኙነቱ ሁለቱንም ማህበረሰቦች ተጠቃሚ እንዲያደርግ የተያዙትን እንቅስቃሴዎች ጥበቡ አሰፋ በቀርብ ያውቃል። ጥበቡ በዩናይትድ ስቴይትስ Blessed Coffee የተባለ ኩባንያ መስርቶ ይሰራል። የተለያዩ የቡና አብቃይ ገበሬዎች ከአለም አቀፍ የቡና ዋጋ ተጠቃሚነታቸውን ለመጨመር እንደሚሰራ ይገልጻል።

ለዚህም በቀጥታ ከማሳ ወደ ዩናይትድ ስቴይስ ቡና ጠጭዎች ምርቱን ለማሸጋገር በመስራት ላይ ነው። በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የኢትዮጵያን ገበያ ከሌሎች አካባቢዎች ጋር ለማገናኘትና አብሮ ለመጠቀም በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ አምራቾች ጋር ሽርክና መፍጠር አለባቸው ይላል።

ዝርዝሩን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

XS
SM
MD
LG